La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 16:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይኸው ድንበር በምዕራብ በኩል ከታፑሐ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርስና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ ለኤፍሬም ነገድ በየወገኑ ርስት ሆኖ የተሰጠው ምድር ይህ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድን​በ​ሩም ከጣፉ ወደ ባሕር እስከ ኬል​ቃን ወንዝ ድረስ ያል​ፋል፥ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ። የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 16:8
10 Referencias Cruzadas  

በዚያም አበኔር ኢያቡስቴን በገለዓድ ግዛቶች፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም ይኸውም በመላው እስራኤል ላይ እንዲነግሥ አደረገ።


የኤፍሬም ዘሮች በሙሉ ወስደው የራሳቸው መኖሪያ ያደረጉት ግዛት ቤትኤልና በዙሪያዋ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞችን ሲሆን፥ በምሥራቅ በኩል እስከ ናዕራን፥ በምዕራብ እስከ ጌዜር፥ እንዲሁም በጌዜር ዙሪያ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞችን ያጠቃልል ነበር፤ እንዲሁም ሴኬምንና ዓያን በዙሪያቸው የሚገኙትንም ታናናሽ ከተሞች ይጨምራል።


ኤፍሬም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከምናሴ ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤


“የምዕራቡ ወሰን የሜድትራኒያን ባሕር ጠረፍ ይሆናል።


ታፑሐ፥ ሔፌር፥


እርሱም በምናሴ ርስት ክልል ውስጥ ያሉትንና ለኤፍሬማውያን የተሰጡትን ከተሞችና መንደሮችንም ይጨምራል፤


የምናሴ የርስት ይዞታ ከአሴር ተነሥቶ በሴኬም በስተ ምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ሚክመታት ይደርስ ነበር፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በማለፍ የዔንታፑዓሕን ሕዝብ ይጨምራል፤


ወደ ዔብሮን፥ ረሖብ፥ ሐሞንና ቃና አልፎ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።