Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ድን​በ​ሩም ከጣፉ ወደ ባሕር እስከ ኬል​ቃን ወንዝ ድረስ ያል​ፋል፥ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ። የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይኸው ድንበር በምዕራብ በኩል ከታፑሐ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርስና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ ለኤፍሬም ነገድ በየወገኑ ርስት ሆኖ የተሰጠው ምድር ይህ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 16:8
10 Referencias Cruzadas  

በገ​ለ​ዓ​ድና በታ​ሲሪ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም፥ በብ​ን​ያ​ምም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሠው።


ግዛ​ታ​ቸ​ውና ማደ​ሪ​ያ​ቸው ቤቴ​ልና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ነዓ​ራን፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ጌዝ​ርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ደግ​ሞም ሴኬ​ምና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መን​ደ​ሮ​ችዋ ድረስ፤


ከም​ና​ሴም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለኤ​ፍ​ሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


“ለባ​ሕ​ርም ዳርቻ ታላቁ ባሕር ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል፤ ይህ የባ​ሕር ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።


የኤ​ጣ​ፋድ ንጉሥ፥


ይኸ​ውም በም​ናሴ ልጆች ርስት መካ​ከል ለኤ​ፍ​ሬም ልጆች ከተ​ለዩ ከተ​ሞች ጋር፥ ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ጋር ነው።


የም​ና​ሴም ልጆች ድን​በር በሐ​ነት ልጆች ፊት ያለው ዴላ​ናታ ነው። በኢ​ያ​ሚ​ንና በኢ​ያ​ሲብ ድን​በር በተ​ፍ​ቶት ምንጭ ላይ ያል​ፋል።


ከዚ​ያም ወደ ኤብ​ሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜ​ማ​ህን፥ ወደ ቀን​ታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደ​ር​ሳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos