“እርሱ ግፍና ችግር ደረሰበት፤ ይሁን እንጂ ምንም አልተናገረም፤ ለመታረድ እንደሚወሰድ ጠቦትና በሸላቾቹ ፊት ጸጥ እንደሚል በግ ዝም አለ እንጂ ምንም አልተናገረም።
ዮሐንስ 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ግቢው ገባና ኢየሱስን “አንተ ከየት ነህ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ግቢው ተመልሶ ኢየሱስን፣ “ከየት ነው የመጣኸው?” በማለት ጠየቀው፤ ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሶም ወደ ገዢው ግቢ ገባና ኢየሱስን “አንተ ከየት ነህ?” አለው። ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ወደ ፍርድ አደባባይ ገባና ጌታችን ኢየሱስን፥ “አንተ ከወዴት ነህ?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሶም ወደ ገዡ ግቢ ገባና ኢየሱስን፦ “አንተ ከወዴት ነህ?” አለው። ኢየሱስ ግን አንድ እንኳ አልመለሰለትም። |
“እርሱ ግፍና ችግር ደረሰበት፤ ይሁን እንጂ ምንም አልተናገረም፤ ለመታረድ እንደሚወሰድ ጠቦትና በሸላቾቹ ፊት ጸጥ እንደሚል በግ ዝም አለ እንጂ ምንም አልተናገረም።
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስን ከቀያፋ ቤት ወደ አገረ ገዢው ግቢ ወሰዱት፤ ጊዜውም ጠዋት ማለዳ ነበር፤ አይሁድ ለፋሲካ በዓል የሚታረደውን በግ መብላት ስለ ነበረባቸው እንዳይረክሱ በማለት ወደ አገረ ገዢው ግቢ ውስጥ አልገቡም።
ጲላጦስም “ታዲያ፥ አንተ ንጉሥ ነኻ?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንኩ አንተ ትላለህ፤ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ልመሰክር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማል” ሲል መለሰ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ምንም እንኳ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ከየት እንደ መጣሁ፥ ወዴትም እንደምሄድ ስለማውቅ ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከየት እንደ መጣሁና ወዴት እንደምሄድ አታውቁም።
ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ድፍረታችሁ ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳኛችሁ ምልክት ነው።
ከዚህ በኋላ ሴቲቱ መጥታ ለባልዋ እንዲህ አለችው፤ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ እኔ ከወዴት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤