በዚህ ጊዜ አባታቸው “ልጆቼን ሁሉ እንዳጣ ትፈልጋላችሁን? ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ለመውሰድ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ!” አለ።
ኢዮብ 7:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ሕይወቴ ከትንፋሽ ያጠረ መሆኑን አስታውስ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ መልካም ነገርን አላይም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕይወቴ ትንፋሽ ያህል እንደ ሆነች ዐስብ፤ ዐይኔም ከእንግዲህ ደስታን አያይም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሕይወቴ እስትንፋስ እንደሆነ አስታውስ፥ ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወቴ እስትንፋስ እንደ ሆነች አስብ፤ ዐይኔም መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ ዳግመኛ አታይም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወቴ እስትንፋስ እንደ ሆነ አስብ፥ ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም። |
በዚህ ጊዜ አባታቸው “ልጆቼን ሁሉ እንዳጣ ትፈልጋላችሁን? ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ለመውሰድ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ!” አለ።
‘እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እኔን በእምነት ባትከተሉ በአረማውያን ሕዝቦች መካከል እበትናችኋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ ተመልሳችሁ ያዘዝኳችሁን ትእዛዞች ብትፈጽሙ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ የተበታተናችሁ ብትሆኑም እንኳ ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን ወደ መረጥሁት ስፍራ እንደገና በመሰብሰብ መልሼ አመጣችኋለሁ’ ስትል ለሙሴ የተናገርከውን ቃል አስብ።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እባክህ አስታውሰኝ፤ እርዳኝም፤ አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ፤ ከትዕግሥትህ ብዛት የተነሣ እንድጠፋ አታድርገኝ፤ ይህም ስድብ የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው።