39 ካለፈ በኋላ እንደማይመለስ ነፋስ፥ ሟች ፍጥረቶች መሆናቸውን አስታወሰ።
39 ወጥቶ የማይመለስ ነፋስ፣ ሥጋ ለባሾች መሆናቸውን ዐሰበ።
39 ወጥቶ የማይመለስ ነፋስ፥ ሥጋም እንደ ሆኑ አሰበ።
ነገ የሚሆነውን አታውቁም፤ ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ለአንድ አፍታ ታይቶ በኋላ እንደሚጠፋ ጉም ናችሁ።
አምላክ ሆይ! ሕይወቴ ከትንፋሽ ያጠረ መሆኑን አስታውስ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ መልካም ነገርን አላይም።
እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
ተስፋ ቈርጬአለሁ፤ መኖርም አልፈልግም፤ የሕይወቴም ዘመን አጭር ስለ ሆነ ተወኝ።
እንደ ሸክላ ዕቃ ከዐፈር እንደ ሠራኸኝ አስብ፤ ታዲያ፥ አሁን መልሰህ እንደ ትቢያ ልታደቀኝ ነውን?
ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው።