ኤርምያስ 48:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብና ከተሞችዋማ እነሆ ተደምስሰዋል፤ የሚያስደስቱ ወጣቶችዋም ለመታረድ ወርደዋል። እኔ ንጉሡ ይህን ተናግሬአለሁ ስሜም ‘የሠራዊት አምላክ’ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓብ ትጠፋለች፤ ከተሞቿም ይወረራሉ፤ ምርጥ ወጣቶቿም ወደ መታረድ ይወርዳሉ፤” ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሞአብና ከተሞችዋ አጥፊው ወጥቶአል፥ የተመረጡትም ጉልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞዓብ ፈርሳለች፤ ከተሞቹዋም ጠፍተዋል፤ የተመረጡትም ጐልማሶችዋ ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብ ፈርሶአል፥ ከተሞቹም ጠፍተዋል፥ የተመረጡትም ጕልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ ንጉሥ። |
“ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ የሚጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው ነኝ፤ በተራሮች መካከል ታቦር፥ በባሕር አጠገብ ቀርሜሎስ ከፍ ብለው እንደሚታዩ እንደዚሁ በእናንተ ላይ ከፍ ብሎ የሚታይ፥ ኀይል ይመጣል።
ወታደሮቻቸውን፥ ወደ ማረጃ ቦታ ወርደው እንደሚታረዱ የዕርድ ኰርማዎች ወስዳችሁ ግደሉ፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ ለባቢሎን ሕዝብ ወዮላቸው!
ነገር ግን ታዳጊያቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱ ራሱ ይረዳቸዋል፤ ሰላምን በምድር ላይ ያወርድላቸዋል፤ በባቢሎን ሕዝብ ላይ ገና መከራን ያመጣባቸዋል።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ በግ ጠቦቶችና እንደ አውራ ፍየሎች ወደ ዕርድ ቦታ እንዲወሰዱ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
“በግብጽ ምድር የላክሁትን ዐይነት መቅሠፍት ላክሁባችሁ፤ ጐልማሶቻችሁ በሰይፍ እንዲሞቱ፥ ፈረሶቻችሁም እንዲማረኩ አደረግሁ፤ በሰፈራችሁ በሞቱ ሰዎች የበድን ግማት አፍንጫችሁን ሞላሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።
ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ሲያጭዱ ለዋሉት ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ፥ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፤ የመከር ሰብሳቢዎቹንም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ሰምቶአል።