Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 51:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ በግ ጠቦቶችና እንደ አውራ ፍየሎች ወደ ዕርድ ቦታ እንዲወሰዱ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 “እንደ ጠቦት፣ እንደ አውራ በግና እንደ ፍየል፣ ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 እንደ ጠቦቶችና እንደ አውራ በጎች እንደ አውራ ፍየሎችም ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እንደ ጠቦ​ቶ​ችና እንደ አውራ በጎች፥ እንደ አውራ ፍየ​ሎ​ችም ወደ መታ​ረድ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 እንደ ጠቦቶችና እንደ አውራ በጎች እንደ አውራ ፍየሎችም ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 51:40
6 Referencias Cruzadas  

ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤ የእግዚአብሔር ጠላቶች እንደ በረሓ አበባ ይረግፋሉ፤ እንደ ጢስም ከዓይን ይሰወራሉ።


ነገር ግን ስለ አንተ በየቀኑ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎችም ተቈጥረናል።


ለመሥዋዕት የቀረቡ የበግና የፍየል ጠቦቶች በሚሠዉበት ጊዜ ደማቸውና ስባቸው ሰይፉን እንደሚሸፍን የእርሱም ሰይፍ በኤዶማውያን ደምና ስብ ይሸፈናል፤ እግዚአብሔር ይህን መሥዋዕት በቦጽራ ከተማ፥ ይህንንም ታላቅ ዕርድ በኤዶም ምድር ያቀርባል።


ሞአብና ከተሞችዋማ እነሆ ተደምስሰዋል፤ የሚያስደስቱ ወጣቶችዋም ለመታረድ ወርደዋል። እኔ ንጉሡ ይህን ተናግሬአለሁ ስሜም ‘የሠራዊት አምላክ’ ነው።


ወታደሮቻቸውን፥ ወደ ማረጃ ቦታ ወርደው እንደሚታረዱ የዕርድ ኰርማዎች ወስዳችሁ ግደሉ፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ ለባቢሎን ሕዝብ ወዮላቸው!


እንደ ቅልብ የባሳን ጠቦትና ሙክት ፍየልና ኰርማ የሆኑትን የኀያላን ሰዎችን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድር ልዑላንንም ደም ትጠጣላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos