እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤
ኤርምያስ 42:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አለቆች፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናንና የሆሻያ ልጅ ዐዛርያስ ሕዝቡም ሁሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቃሬያን ልጅ ዮሐናንና የሆሻያን ልጅ ያእዛንያን ጨምሮ፣ የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጭፍራ አለቆችም ሁሉ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የሆሻያም ልጅ ያእዛንያ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ቀረቡ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጭፍራ አለቆችም ሁሉ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የሐናንያ ልጅ ኢዛንያስ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጭፍራ አለቆችም ሁሉ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የሆሻያም ልጅ ያእዛንያ ሕዝብም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ቀረቡ፥ |
እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
በእስራኤል ስም የምትጠሩ፥ ከይሁዳ ወገን የሆናችሁ፥ እናንተ የያዕቆብ ልጆች! ይህን ስሙ። እናንተ በታማኝነትና በእውነት ሳይሆን፥ የእስራኤልን አምላክ እናመልካለን ትላላችሁ፤ በእግዚአብሔር ስምም ትምላላችሁ።
ንጉሥ ሴዴቅያስ የሼሌምያን ልጅ የሁካልንና የማዕያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እኔ ወደ ኤርምያስ ልኮ “ስለ ሕዝባችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይ” ብለው እንዲጠይቁኝ አደረገ።
ስለዚህ የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የታንሑሜት ልጅ ሠራያ፥ ከነጦፋ የዔፋይ ልጆች፥ ከማዕካም የዛንያ ከሰዎቻቸው ሁሉ ጋር በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ገዳልያ መጡ።
ከዚህ በኋላ ዮሐናንና ከእርሱ ጋር ያሉት የሠራዊቱ መሪዎች፥ እስማኤል ገዳልያን ከገደለ በኋላ ከምጽጳ ማርኮ የወሰዳቸውን ወታደሮች፥ ሴቶች፥ ሕፃናትና ጃንደረቦች ሁሉ መለሱ።
ከዚያ በኋላ የሆሻያ ልጅ ዐዛርያስ፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናንና ትዕቢተኞች የሆኑ ሌሎችም ሰዎች ሁሉ እንዲህ አሉ፦ “ውሸትህን ነው፤ አምላካችን እግዚአብሔር እኛ ወደ ግብጽ ሄደን እዚያ እንዳንኖር ትነግረን ዘንድ አላከህም፤
በይሁዳ ከስደት ከተረፉት መካከል ወደ ግብጽ ወርደው በዚያ ለመኖር የወሰኑትን ሁሉ እንዲጠፉ አደርጋለሁ፤ ከትልቅ እስከ ትንሽ በጦርነት ወይም በረሀብ በግብጽ አገር ይሞታሉ። እነርሱም ለሕዝቦች አስደንጋጭ ይሆናሉ፤ ሕዝብም ሁሉ ይዘባበትባቸዋል፤ ስማቸውንም መራገሚያ ያደርጉታል።
ስለዚህ እርሻቸውን ሁሉ ለሌሎች ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ ሚስቶቻቸውንም ሌሎች ወንዶች እንዲቀሙአቸው አደርጋለሁ፤ ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች እያንዳንዱ ሰው በማታለል ጥቅምን ያግበሰብሳል፤ ነቢያትና ካህናት ሳይቀሩ ሕዝቡን ያታልላሉ፤
የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ወደ ላይ አንሥቶ በምሥራቅ ትይዩ ወደ ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ወደ አለው ወደ ምሥራቁ በር አመጣኝ፤ እዚያም በቅጽር በሩ አጠገብ ኻያ አምስት ሰዎችን አየሁ፤ በእነርሱም መካከል የሕዝብ መሪዎች የሆኑት የዐዙር ልጅ አዛንያና የበናያ ልጅ ፈላጥያ ይገኙባቸዋል።
ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤
የሻፋንን ልጅ አዛንያን ጨምሮ ሰባ የእስራኤላውያን መሪዎች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጥና ይዞ ነበር፤ ከጥናውም መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጢስ ይወጣ ነበር፤