ዳዊት ከኮረብታው ጫፍ ባሻገር ገና ጥቂት እንደ ሄደ ጺባ ተብሎ የሚጠራው የመፊቦሼት አገልጋይ በድንገት አገኘው፤ እርሱም ሁለት መቶ ሙልሙል ዳቦ፥ አንድ መቶ የዘቢብ ጥፍጥፍ፥ አንድ መቶ እስር ፍራፍሬና በወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ የተጫኑ ሁለት አህዮች ይነዳ ነበር፤
ኤርምያስ 40:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም በዚህቹ በምጽጳ ከእናንተ ጋር ስለምኖር ባቢሎናውያን በሚመጡበት ጊዜ የእናንተ ወኪል ሆኜ እቆምላችኋለሁ፤ እናንተ ግን በምትኖሩባቸው መንደሮች ሁሉ የወይኑን ዘለላ፥ የወይራውን ዘይትና የሌላውን ተክል ፍሬ ሰብስባችሁ አከማቹ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ራሴ ወደ እኛ በሚመጡት በባቢሎናውያን ፊት ልቆምላችሁ፣ በምጽጳ እቀመጣለሁ፤ እናንተ ግን ወይን፣ የበጋ ፍሬና ዘይት አምርቱ፤ በማከማቻ ዕቃዎቻችሁ ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞች ተቀመጡ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፥ እነሆ፥ ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት ለእናንተ ዋስትና ለመቆም በምጽጳ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይንንና የበጋ ፍሬ ዘይትንም አከማቹ፥ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፥ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በመሴፋ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይኑንና ፍሬውን፥ ዘይቱንም አከማቹ፤ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፥ እነሆ፥ ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በምጽጳ እኖራለሁ፥ እናንተ ግን ወይንንና የበጋ ፍሬ ዘይትንም አከማቹ፥ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፥ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ። |
ዳዊት ከኮረብታው ጫፍ ባሻገር ገና ጥቂት እንደ ሄደ ጺባ ተብሎ የሚጠራው የመፊቦሼት አገልጋይ በድንገት አገኘው፤ እርሱም ሁለት መቶ ሙልሙል ዳቦ፥ አንድ መቶ የዘቢብ ጥፍጥፍ፥ አንድ መቶ እስር ፍራፍሬና በወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ የተጫኑ ሁለት አህዮች ይነዳ ነበር፤
ስለ ያዕዜር እንደማለቅስ ስለ ሲብማ የወይን ሐረጎችም አለቅሳለሁ፤ ስለ ሐሴቦንና ስለ ኤልዓሌ እንባዬ ይረግፋል፤ ሕዝቡ የሚደሰትበት መከር አልተገኘባቸውም፤
ስለዚህም ተበታትነው የሚኖሩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ትተው ወደ ይሁዳ ተመለሱ፤ በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ገዳልያም መጥተው እጅግ ብዙ የሆነ የወይን ዘለላና የሌላውንም ተክል ፍሬ በመሰብሰብ አከማቹ።
ከዚህም በኋላ ዮሐናንና የሠራዊት አለቆች በይሁዳ የተረፉትን በሙሉ ወደ ግብጽ ወሰዱ፤ ይኸውም ከዚህ በፊት በአሕዛብ መካከል ተበታትነው ከቈዩ በኋላ እንደገና ወደ ይሁዳ አገር ተመልሰው የነበሩትን ሕዝብ ማለትም፥
ለያዕዜር ሕዝብ ከማለቅሰው ይበልጥ ለሲብማ ሕዝብ እየጮኽኩ አለቅሳለሁ፤ የሲብማ ከተማ ሆይ! እንቺ ቅርንጫፎችዋ ሙት ባሕርን አልፎ እስከ ያዜር እንደሚደርስ የወይን ተክል ነሽ፤ ነገር ግን በጐመራው ፍሬሽና በወይን ዘለላሽ ላይ አጥፊው መጥቷል።
የመከር ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ከተቃረመ በኋላ ሊበላ የሚፈልገውን የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ስለ ሆንኩ ወዮልኝ! እኔ የምመኘውም አስቀድሞ የደረሰው የበለስ ፍሬ የለም።
ነገር ግን የአንተ ረዳት የሆነው የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደ ምድሪቱ ይገባል፤ ምድሪቱን ይወርሱ ዘንድ እስራኤልን የሚመራ እርሱ ስለ ሆነ አበረታታው።’