እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ ይህም ያደረጉት በደል ቊጣዬን አነሣሥቶአል፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተነሣሣው ቊጣዬም ይፈጸማል እንጂ አይበርድም፤
ኤርምያስ 4:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የይሁዳ ሕዝብና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የልባችሁን ክፋት ገርዛችሁ አእምሮአችሁን በማንጻት ሁለንተናችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ይህን ባታደርጉ ግን በክፉ ሥራችሁ ምክንያት ቊጣዬ እንደ እሳት ይነዳል፤ ቊጣዬም ከነደደ ማንም ሊያጠፋው አይችልም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤ አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ ሊገታውም የሚችል የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ! ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለጌታ እራሳችሁን ግረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳይነድ ለአምላካችሁ ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ። |
እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ ይህም ያደረጉት በደል ቊጣዬን አነሣሥቶአል፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተነሣሣው ቊጣዬም ይፈጸማል እንጂ አይበርድም፤
የእስራኤል ብርሃን እግዚአብሔር ራሱ እሳት ይሆንባቸዋል፤ የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ራሱ በአንዲት ቀን ኲርንችቱንና እሾኹን ሳያስቀር ሁሉን በልቶ እንደሚጨርስ የእሳት ነበልባል ይሆናል።
ከብዙ ዘመናት በፊት የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚቃጠልበት ቦታ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ያም ቦታ ሰፊና ጥልቅ ሆኖ ብዙ እንጨት ተከማችቶበት ነበር፤ እንደ ዲን ጅረት የሚፈሰው የእግዚአብሔር እስትንፋስ እሳቱን ያቀጣጥለዋል።
እግዚአብሔር አስፈሪ በሆነው ቊጣና መዓቱ ሕዝቡን እንደሚቀጣ የተናገረ በመሆኑ ምናልባት በመጸጸት ከክፉ ሥራቸው ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ይለምኑት ይሆናል።”
እነሆ በአሁኑ ጊዜ ምድራችሁ ፍርስራሽ ሆናለች፤ የሚኖርባትም የለም፤ ምድሪቱ አጸያፊ ሆናለች፤ ሕዝብም ሁሉ እንደ ተረገመች ይቈጥሩአታል፤ እግዚአብሔር የዐመፅና የክፋት ሥራችሁን ሁሉ አይታገሥም።
የግብጽ፥ የይሁዳ፥ የኤዶም፥ የአሞን፥ የሞአብና በበረሓ ጠረፍ የሚኖሩ የግንባራቸውን ግራና ቀኝ ጠጒር የተላጩ ሕዝቦች እንዲሁም የእስራኤል ሕዝብ ከልባቸው ያልተገረዙ ስለ ሆኑ ሁሉንም በአንድ ዐይነት እቀጣለሁ።”
ኢየሩሳሌም ሆይ! ሴሰኛነትሽ አርክሶሻል፤ እኔ እንኳ ላነጻሽ ብፈቅድ አንቺ ከርኲሰትሽ አልነጻሽም። የቊጣዬ ኀይል እስከሚገለጥብሽ ድረስ ዳግመኛ ንጹሕ አትሆኚም።
ስብንና ደምን ለእኔ የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ በምታቀርቡበት ጊዜ ሊታዘዙኝ ፈቃደኞች ያልሆኑትን ያልተገረዙ ባዕዳን ወደ ተቀደሰው ስፍራዬ በማስገባት ቤተ መቅደሴን አርክሳችኋል፥ በረከሰውም ተግባራችሁ ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሳችኋል።
በሩቅ ያሉት ታመው ይሞታሉ፤ በቅርብ ያሉትም በጦርነት ይገደላሉ፤ ከዚያ የሚተርፉትም በራብ ያልቃሉ፤ በዚህም ዐይነት ኀይል የተሞላበትን ቊጣዬን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።
ይልቅስ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ አለበለዚያ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደ እሳት ሆኖ ያጋያቸዋል፤ የቤትኤልንም ኗሪዎች እሳት ይበላቸዋል፤ እሳቱን የሚያጠፋላቸውም አይገኝም።
አለበለዚያ ግን ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው ገለባ ትሆናላችሁ፤ እንደ እሳት የሚነደው የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣባችኋል፤ ኀይለኛው የእግዚአብሔር የቊጣ ቀን ይመጣባችኋል።
አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተና ለልጆችህ ታዛዥ ልብ ይሰጣል፤ ስለዚህም እርሱን በፍጹም ልብህ ትወደዋለህ፤ በዚያችም ምድር በሕይወት ትኖራለህ።
በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤ እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤ ምድርንና ምርቱን ይበላል። ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል።
በእርሱም በማመናችሁ ተገርዛችኋል፤ ይህም መገረዛችሁ ኃጢአተኛውን የሥጋ ባሕርይ ለማስወገድ በክርስቶስ የተደረገ ነው እንጂ በሰው እጅ የተደረገ አይደለም።