አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አዎ! አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ራስህን ለኃጢአት ሸጠሃል፤
ኤርምያስ 38:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ መኳንንቱ ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው ሞት ይገባዋል፤ በእንደዚህ ያለ አነጋገር እየተናገረ በከተማይቱ የቀሩት ወታደሮች ወኔ እንዳይኖራቸው አድርጎአል፤ በከተማይቱ ሰው ሁሉ ላይ የሚያደርገው ይኸው ነው፤ ሕዝቡን ለመጒዳት እንጂ ለመርዳት የሚፈልግ ሰው አይደለም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኳንንቱም ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ይህ ሰው በሚናገረው ነገር በዚህች ከተማ የቀሩትን ወታደሮችና ሕዝቡንም ሁሉ ተስፋ የሚያስቈርጥ ስለ ሆነ መሞት አለበት፤ ይህ ሰው የሕዝቡን መጥፋት እንጂ መልካም ነገር አይሻም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹም ንጉሡን፦ “ይህን የመሰለውን ቃላት እየነገራቸው የሕዝቡን ሁሉ እጅ በዚህችም ከተማ የቀሩትን የወታደሮቹን እጅ እያደከመ ነውና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፤ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹም ንጉሡን፥ “ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚያች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ፥ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው ይገደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹም ንጉሡን፦ ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚህች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፥ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና አሉት። |
አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አዎ! አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ራስህን ለኃጢአት ሸጠሃል፤
ንጉሥ ኢዮአስ በዘካርያስ ላይ በተደረገው ሤራ ተባባሪ ሆነ፤ ሕዝቡም በንጉሡ ትእዛዝ ዘካርያስን በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
“ከግርማዊነትዎ ዘንድ የመጡት አይሁድ እዚህ ኢየሩሳሌም የደረሱ መሆናቸው በግርማዊነትዎ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ያቺን ዐመፀኛና ክፉ ከተማ እንደገና በመሥራት ላይ ናቸው፤ ቅጽሮቹን በመጠገንና የቤተ መቅደስዋንም መሠረት በመጣል ላይ ናቸው።
“በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገርክ እንደ ሆነ እንገድልሃለን” ብለው የኤርምያስን ሕይወት ለማጥፋት ስለሚፈልጉት ስለ አናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
አምላክ ሆይ! እነርሱ እኔን ለመግደል የሸረቡትን ሤራ ታውቀዋለህ፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ይቅር አትበል፤ ኃጢአታቸውም እንዲሰረይላቸው አታድርግ፤ በፊትህ እንዲሸነፉና በብርቱ ቊጣህ እንዲወድቁ አድርግ።”
ካህናቱና ነቢያቱ ለመሪዎቹና ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው የተናገረውን ሁሉ እናንተ ራሳችሁ ሰምታችሁታል፤ በከተማችን ላይ ክፉ የትንቢት ቃል በመናገሩ ሞት ይገባዋል።”
ተማርካችሁ ሄዳችሁ እንድትኖሩባቸው ላደረግኋቸው ከተሞችም ዕድገት መልካም ነገርን ተመኙ፤ ስለ እነርሱም መልካም ኑሮ ወደ እኔ ጸልዩ፤ እነርሱ መልካም ኑሮ ቢኖሩ እናንተም መልካም ኑሮን ትኖራላችሁ።
ስለዚህም ንጉሥ ሴዴቅያስ “እኔ አልገድልህም፤ ለሚገድሉህም ሰዎች አሳልፌ ላልሰጥህ ሕይወትን በሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ!” በማለት በምሥጢር ቃል ገባልኝ።
ባለ ሥልጣኖቹ እኔ ከአንተ ጋር መነጋገሬን የሰሙ እንደ ሆነ መጥተው ምን እንደ ተባባልን ይጠይቁሃል፤ ሁሉን ነገር ባትነግራቸው እንገድልሃለን ብለው ያስፈራሩሃል፤
የቤትኤል ካህን የሆነው አሜስያስ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም ላከ፦ “እነሆ አሞጽ በእስራኤል ሕዝብ መካከል ሆኖ በአንተ ላይ እያሤረብህ ነው፤ ሕዝቡ የእርሱን ንግግር ሊታገሥ አይችልም።
እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።”
ነገር ግን እነርሱን ባጡአቸው ጊዜ ኢያሶንንና አንዳንድ አማኞችን ለከተማው ባለሥልጣኖች ለማቅረብ እየጐተቱ ወሰዱአቸው፤ እንዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ “እነዚህ ዓለምን ሁሉ ያወኩ ሰዎች አሁን ደግሞ ወደዚህ መጥተዋል!
ይህን አንተ የምትከተለውን የሃይማኖት ክፍል በየቦታው ሰዎች እንደሚቃወሙት እናውቃለን፤ ስለዚህ የአንተ አሳብ ምን እንደ ሆነ መስማት እንፈልጋለን።”