ንጉሥ ኢኮንያን ከእናቱ፥ ከልዑላን መሳፍንቱ፥ ከጦር አዛዦቹና ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች ጋር ቀርቦ ለባቢሎናውያን እጁን ሰጠ፤ ናቡከደነፆር በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ያዘው፤
ኤርምያስ 22:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኢዮአቄም ልጅ ለኢኮንያን እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ “እኔ ሕያው አምላክ አንተ በቀኝ እጄ እንደሚገኝ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ አውልቄ እጥልሃለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሕያውነቴ እምላለሁ”፤ ይላል እግዚአብሔር “የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ የቀለበት ማኅተም ብትሆን እንኳ ኖሮ፣ አውልቄ እጥልሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ የማኅተም ቀለበት ቢሆን ኖሮ እንኳ፥ ከዚያ አውልቄ እጥልህ ነበር፥ ይላል ጌታ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔ ሕያው ነኝ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን ሆይ፥ አንተን በሰወርሁበት ቀኝ እጄ እንዳለ ማሕተም ነበርህ፤ እንግዲህ ወዲህ ግን እንደማትኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ ማኅተም ቢሆን ኖሮ እንኳ፥ ከዚያ እነቅልህ ነበር፥ ይላል እግዚአብሔር፥ |
ንጉሥ ኢኮንያን ከእናቱ፥ ከልዑላን መሳፍንቱ፥ ከጦር አዛዦቹና ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች ጋር ቀርቦ ለባቢሎናውያን እጁን ሰጠ፤ ናቡከደነፆር በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ያዘው፤
ናቡከደነፆር ኢኮንያንን አስሮ ከነእናቱ ከሚስቶቹ፥ ባለሟሎቹ ከሆኑ ባለሥልጣኖችና ከይሁዳ ታላላቅ ሰዎች ጋር በአንድነት ሰብስቦ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።
ኢኮንያን በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ከዐሥር ቀን ገዛ፤ እርሱም ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ።
በዘለዓለማዊ ፍቅር በልብህ ውስጥ እንደ ማኅተም አትመኝ፤ በክንድህም እንደ ማኅተም እኔን ብቻ ያዘኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት፤ ቅናትም እንደ መቃብር የከፋች ናት፤ የእሳትዋ ወላፈን እንደ እግዚአብሔር ወላፈን ነው።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ንጉሥ ኢኮንያን ከተጣለ በኋላ ማንም እንደማይፈልገው ሰባራ ገንቦ መሆኑ ነውን? እርሱና ልጆቹ ተማርከው ወደማያውቁት አገር የተወሰዱት ለምንድን ነው?”
“የይሁዳ ነገሥታት ቤተ መንግሥት የገለዓድን አገርና የሊባኖስን ተራራዎች ያኽል ለእኔ የተዋበ ነው፤ ነገር ግን ማንም የማይኖርበት ባድማ አደርገዋለሁ።
እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ፍሬ ቅርጫቶችን አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮአቄም ልጅ የሆነውን የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያንን ከይሁዳ መሪዎች፥ ከእጅ ጥበብ ባለሞያዎችና ከሌሎችም ብልኀተኞች ሠራተኞች ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን አስሮ ከወሰደ በኋላ ነው።
እንዲሁም የኢዮአቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ወደ ባቢሎን ተሰደው ከሄዱት ከይሁዳ ሕዝብ ጋር መልሼ አመጣዋለሁ፤ አዎ! የባቢሎንን ንጉሥ የአገዛዝ ቀንበር እሰብራለሁ፤’ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ደብዳቤውንም የጻፍኩት ንጉሡ ኢኮንያን፥ እቴጌይቱ እናቱና የቅርብ አገልጋዮቹ፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መሪዎች፥ የእጅ ጥበብ ሠራተኞችና ሙያተኞች ሁሉ ተማርከው ከተወሰዱ በኋላ ነው፤
አገልጋዬ ዘሩባቤል ሆይ! እኔ አንተን መርጬሃለሁ፤ አንድ ቀን መሪ እንድትሆን አንተን ለይቼ እንደ ማኅተም ቀለበቴ አደርግሃለሁ፤” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።