Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ኢዮአቄም ደግሞ ኢኮንያንና ጼዴቅያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የኢዮአቄም ዘሮች፤ ልጁ ኢኮንያ፣ ልጁ ሴዴቅያስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የኢዮአቄምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮንያንና ልጁ ሴዴቅያስ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮ​ን​ያን፥ ልጁ ሴዴ​ቅ​ያስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የኢዮአቄምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮንያን፥ ልጁ ሴዴቅያስ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 3:16
12 Referencias Cruzadas  

ናቡከደነፆር በኢኮንያን ምትክ ማታንያ ተብሎ የሚጠራውን የዮአኪንን አጐት በይሁዳ አነገሠ፤ ስሙንም በመለወጥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው።


ኢዮአቄም ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢኮንያን ነገሠ።


ኢኮንያን በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ነሑሽታ ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ የሆነው የኤልናታን ልጅ ነበረች።


ዮርማሮዴቅ ኤዊልመሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከእስራት በመፍታት ምሕረት አደረገለት፤ ይህም የሆነው ኢኮንያን በእስረኛነት ተማርኮ በሄደ በሠላሳ ሰባት ዓመቱ በዐሥራ ሁለተኛው ወር በሃያ ሰባተኛው ቀን ነው።


የኢዮስያስም ልጆች በኲሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛው ኢዮአቄም፥ ሦስተኛው ሴዴቅያስና አራተኛው ሻሉም ናቸው፤


የባቢሎን ምርኮኛ የነበረው የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ ማልኪራም፥ ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማዕና ነዳብያ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።


የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለቤተ መቅደሱ ስላዘነ ያስጠነቅቁአቸው ዘንድ ነቢያትን መላልሶ መላክን ቀጠለ።


ኢኮንያን በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ከዐሥር ቀን ገዛ፤ እርሱም ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ።


ለኢዮአቄም ልጅ ለኢኮንያን እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ “እኔ ሕያው አምላክ አንተ በቀኝ እጄ እንደሚገኝ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ አውልቄ እጥልሃለሁ፤


እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ንጉሥ ኢኮንያን ከተጣለ በኋላ ማንም እንደማይፈልገው ሰባራ ገንቦ መሆኑ ነውን? እርሱና ልጆቹ ተማርከው ወደማያውቁት አገር የተወሰዱት ለምንድን ነው?”


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮስያስን ልጅ ሴዴቅያስን የኢዮአቄም ልጅ በነበረው በኢኮንያን ምትክ በይሁዳ ላይ አነገሠው።


ኢዮስያስ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ባቢሎን ተማርከው በሄዱበት ዘመን ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos