ኤርምያስ 2:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የያዕቆብ ልጆች የሆናችሁ፤ የእስራኤል ነገድ ሁሉ! እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ስሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ወገን ሁላችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። |
‘የይሁዳ ነገሥታትና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምነግራችሁን አድምጡ፤ እነሆ በጆሮው ለሚሰማው ሰው ሁሉ የሚዘገንን መቅሠፍት አመጣለሁ።
እስራኤል ሆይ! አንቺ እንደ መከር መጀመሪያ ፍሬ ለእኔ የተለየሽ ነበርሽ፤ ለእኔም የተቀደስሽ ርስት ሆነሽ ነበር፤ ስለዚህም አንቺን መጒዳት በሚፈልጉት ሁሉ ላይ መከራና መቅሠፍት አመጣሁባቸው።’ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እነሆ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኔ ርቀው የሄዱት በኔ ላይ ምን ጥፋት አግኝተው ነው? እነርሱም ከንቱ የሆኑትን ጣዖቶች በማምለካቸው ራሳቸውን ከንቱዎች አደረጉ።
“እነዚህ ሕዝቦች፦ ‘እግዚአብሔር የመረጣቸውን እነዚያን ሁለት መንግሥታት ትቶአቸዋል’ ብለው ሕዝቤን በመናቅ በሕዝብነት እንደማያውቁአቸው አላስተዋልክምን?”
በዚህች ምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እርሱ የሚልህን ሁሉ ስማ፦ “በምድሪቱ ላይ ታማኝነትና ፍቅር እግዚአብሔርንም ማወቅ ጠፍቶአል።