ኤርምያስ 2:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሂድና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በመጀመሪያ በምድረ በዳ ምንም በማያበቅልበት ትከተሉኝ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ ለሙሽራው የምታሳየውን ፍቅርና ታማኝነት ለኔም ታሳይ እንደ ነበረ አስታውሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሂድና ጮኸህ ይህን ለኢየሩሳሌም ጆሮ አሰማ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት፣ በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ፣ በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር፣ እንዴት እንደ ተከተልሽኝ አስታውሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮዎች ላይ አውጅ፥ እንዲህም በል፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ጽኑ ፍቅር የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስታውሼዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሂድ፤ እንዲህ ብለህ በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት፥ የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ፥ እንዲህም በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ። |
እግዚአብሔር በእንዴት ያለ ታላቅ ኀይል ግብጻውያንን እንዳሸነፈ እስራኤላውያን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴ አመኑ።
ከዚህም በኋላ ሙሴ እንዲህ አለ፦ “በእርሱ ላይ ማጒረምረማችሁን ስለ ሰማ በማታ የምትበሉትን ሥጋና በማለዳ ደግሞ የፈለጋችሁትን ያኽል እንጀራ የሚሰጣችሁ እግዚአብሔር ነው፤ እኛ ምንድን ነን? በእኛ ላይ ስታጒረመርሙ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረማችሁ ነው።”
እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት! ንጉሥ ሰሎሞንን ለማየት ኑ፤ እርሱ እጅግ በተደሰተበት በሠርጉ ቀን እናቱ በራሱ ላይ የደፋችለትን ዘውድ ጭኖአል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ድምፅህን ሳትቈጥብ ጩኽ! ድምፅህ እንደ እምቢልታ ከፍ ይበል! ለሕዝቤ ለእስራኤል ዐመፃቸውንና ኃጢአታቸውን ንገራቸው።
ከዚያን በኋላም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ወደ ይሁዳ ከተሞችና ወደ ኢየሩሳሌም መንገዶች ሄደህ ቃል ኪዳኔን እንዲያዳምጡና ትእዛዞቼን እንዲፈጽሙ በማሳሰብ ቃሌን ዐውጅላቸው፤
እኔ እነርሱን ከምድረ ግብጽ አወጣኋቸው፤ በምድረ በዳ መራኋቸው፤ ጐድጓዳማ በሆነ መንገድ ድርቅና ጨለማ በበዛበት በረሓ፥ ማንም በማይኖርበትና በማይመላለስበት ምድር አሳለፍኳቸው፤ እነርሱ ግን ‘ይህን ሁሉ ያደረገልን አምላክ ወዴት ነው?’ ብለው እንኳ አልጠየቁም።
እጅግ አጸያፊ በሆነ የአመንዝራነት ኑሮሽ የልጅነትሽን ሁኔታ አላስታወስሽውም፤ ይህም ማለት ራቁትሽን በደም ተነክረሽ ስትንፈራገጪ የነበርሽበት ጊዜ ፈጽሞ ትዝ አላለሽም።”
“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
ክብርናዋን ባጣችበት በግብጽ የጀመረችውን አመንዝራነት ቀጥላለች፤ ከልጃገረድነትዋ ጊዜ ጀምሮ ወንዶች ሁሉ እርስዋን እንደ አመንዝራ በመቊጠር ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ።
የቀድሞውን የወይን ተክል እመልስላታለሁ፤ የመከራንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤ እዚያም ከግብጽ ስትወጣ በወጣትነትዋ ወራት በነበራት ሁኔታ በደስታ ትዘምራለች።
ፍቅረኞችዋን ተከትላ ትሄዳለች፤ ነገር ግን ልትደርስባቸው አትችልም፤ ትፈልጋቸዋለች፤ ነገር ግን አታገኛቸውም፤ ከዚህ በኋላ “ከአሁኑ ኑሮዬ ይልቅ የዱሮው ይሻለኛል፤ ስለዚህ ወደ ቀድሞው ባሌ እሄዳለሁ” ትላለች።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና ሕጌን ስለ ተላለፉ በቤቴ ላይ ጠላት እንደ ጆፌ አሞራ ያንዣበበ ስለ ሆነ የማስጠንቀቂያ መለከት ንፉ!”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤልን ባገኘሁ ጊዜ የወይን ዘለላን ከምድረ በዳ እንደ ማግኘት ነበር፤ የቀድሞ አባቶቻችሁን ባየሁ ጊዜ ቀድሞ የጐመራውን የበለስ ፍሬ እንደማየት ነበር፤ ወደ በዓል ጴዖር በደረሱ ጊዜ ግን ራሳቸውን ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ለይተው አቀረቡ፤ እነርሱም እንደዚያ እንደሚወዱት ጣዖት የረከሱ ሆኑ።
“ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።”
“በእርግጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ብዙ በረከት ሰጥቶአችኋል፤ በዚህ በሰፊው በረሓ በሄዳችሁበት ሁሉ ተንከባክቦአችኋል፤ በእነዚህ በአርባ ዓመቶች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለ ነበረ ምንም የጐደለባችሁ ነገር አልነበረም።
አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።
እናንተ ከዳተኞች! ዓለምን የሚወድ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑን አታውቁምን? እንግዲህ ዓለምን የሚወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑ ነው።