ኤርምያስ 19:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ እንድነግራቸው ያዘዘኝም ቃል ይህ ነው፥ “ይህ የተሰበረ የሸክላ ገንቦ ተመልሶ ሊጠገን እንደማይችል፥ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ በዚሁ ዐይነት እሰባብራለሁ፤ ሰዎች ሙታናቸውን የሚቀብሩበት ሌላ ስፍራ ስለማይገኝ በቶፌት ይቀብሩአቸዋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪው ዕቃ እንደሚሰባበር ዳግመኛም ሊጠገን እንደማይችል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ትላቸዋለህ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ማድጋ እንደሚሰባበር ደግሞም ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀበሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ትላቸዋለህ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪው ዕቃ እንደሚሰባበር ደግሞም ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፥ የሚቀብሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ። |
ከተሰባበረ በኋላ ለእሳት መጫሪያ ወይም ለውሃ መጥለቂያ የሚሆን ከፍ ያለ ገል እንኳ ከመካከሉ እንደማይገኝበት ተንኰታኲቶ እንደሚወድቅ የሸክላ ዕቃ ትሆናላችሁ።”
ያን ጊዜ አባቶችንና ልጆቻቸውን ሁሉንም እንደ ማድጋ እርስ በርሳቸው አጋጫቸዋለሁ፤ ምንም ዐይነት ሐዘኔታ፥ ርኅራኄ ወይም ምሕረት እነርሱን ከማጥፋት ሊያግደኝ አይችልም።”
“እናንተ መሪዎች አልቅሱ፤ እናንተ የሕዝብ ጠባቂዎች ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ዋይ፥ ዋይ!’ በሉ፤ በዐመድ ላይ እየተንከባለላችሁ እዘኑ፤ ሁላችሁም የምትታረዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ ውድ የሆነ የሸክላ ዕቃ ሲወድቅ ተሰብሮ እንደሚበታተን፥ እናንተም ትበታተናላችሁ።
ይህ ነቢይ ወደ እኛ ቀረበ፤ የጳውሎስን መታጠቂያ ወስዶ የገዛ እጆቹንና እግሮቹን አሰረና “መንፈስ ቅዱስ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ እንደዚህ አስረው ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል ይላል” አለ።