ኤርምያስ 13:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ተናግሮአልና፤ ትዕቢታችሁን አስወግዳችሁ ስሙት፤ በጥንቃቄም አድምጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ተናግሯልና፣ ስሙ፤ ልብ በሉ፤ ትዕቢተኛም አትሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስሙ፥ አድምጡም፤ ጌታ ተናግሮአልና አትታበዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስሙ፤ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና አትታበዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስሙ፥ አድምጡ፥ እግዚአብሔር ተናግሮአልና አትታበዩ። |
ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ በጥንቃቄ ልታረጋግጡ ይገባል፤ ይኸውም እኔን ብትገድሉኝ፥ እናንተና የዚህ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ሁሉ ንጹሕ ሰው በመግደላችሁ በደለኞች ሆናችሁ ትገኛላችሁ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ እንድሰጣችሁ ወደ እናንተ የላከኝ በእርግጥ ራሱ እግዚአብሔር ነው።”
እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ! በይሁዳም ምድር የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ! ለመሆኑ ይህን የመሰለ ነገር በዘመናችሁ ወይም በቀድሞ አባቶቻችሁ ዘመን ተደርጎ ያውቃልን?