Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 16:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር ትምክሕተኞችን ሁሉ ይጸየፋል፤ ከቅጣት እንዲያመልጡም አያደርጋቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር በልብ የሚታበዩትን ሁሉ ይጸየፋል፤ እነርሱም ከቅጣት እንደማያመልጡ በርግጥ ዕወቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በልቡ የታበየ ሁሉ በጌታ ዘንድ ርኩስ ነው፥ እጅ በእጅም ሳይቀጣ አይቀርም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የደግ መንገድ መጀመሪያ እውነት መሥራት ነው፥ እርሱም መሥዋዕትን ከመሠዋት ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 16:5
14 Referencias Cruzadas  

በእርግጥ ክፉ ሰዎች መቀጣታቸው የማይቀር ነው፤ ደጎች ግን ይድናሉ።


ክፉ ነገርን መጥላት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ እኔ ትዕቢትንና ዕብሪትን እጠላለሁ፤ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን አልወድም


ሆኖም መጽሐፍ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ስለሚል እግዚአብሔር የሚሰጠው ጸጋ ከሁሉም ይበልጣል።


በጥንቃቄ ሁሉን ተመልክተህ አሳፍራቸው፤ ክፉዎችንም ባሉበት ስፍራ አጥፋቸው።


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


“የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሁሉ ሳይቀጣው አያልፍም።


ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ግንኙነት የሚያደርግ እንደዚሁ ነው፤ የሌላውን ሰው ሚስት የሚነካ ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም።


እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ ምክንያት አለው፤ የክፉዎችም መጨረሻ ጥፋት ነው።


በፍቅርና በእምነት ኃጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፉ ነገር ይርቃል።


እግዚአብሔር ተናግሮአልና፤ ትዕቢታችሁን አስወግዳችሁ ስሙት፤ በጥንቃቄም አድምጡት።


ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ፤ ኩራተኞችም ይቀላሉ፤ እግዚአብሔር ብቻ በክብር ከፍ ከፍ ይላል፤


የሠራዊት አምላክ ትዕቢተኞችና ኩራተኞች የሚዋረዱበትን ቀን ወስኖአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios