ኢሳይያስ 40:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ተማምነው የሚኖሩ ግን ኀይላቸው ይታደስላቸዋል። እንደ ንሥር በክንፍ ይበራሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፥ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፥ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፥ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። |
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አገልጋዮችና ገረዶች የአሳዳሪዎቻቸውን እጅ እንደሚጠባበቁ ሁሉ እኛም እስክትምረን ድረስ የአንተን ምሕረት ለማግኘት እንጠባበቃለን።
“ ‘እኔ እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ያደረግኹትንና ንስር ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ እንደምትሸከም እኔም እናንተን እስከዚህ ስፍራ እንዴት ወደ እኔ እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል፤
በወዳጅዋ ትከሻ ላይ ደገፍ ብላ ከበረሓ የምትመጣ ይህች ማን ናት? ዱሮ እናትህ አንተን አምጣ በወለደችበት በፖም ዛፍ ሥር ቀስቅሼ አስነሣሁህ።
ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።
የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመመለስና በማረፍ ደኅንነትን ታገኛላችሁ፤ ጸጥ በማለትና በመታመን ኀይል ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ።
ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በደሴቶች የምትኖሩ ሕዝቦች! ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! ሕዝቦች ኀይላቸውን ያድሱ፤ ወደ ፊትም ቀርበው ይናገሩ፤ በፍርድ ሸንጎ በአንድነት እንገናኝ።
ከጥንት ጀምሮ ተስፋቸውን በእርሱ አድርገው ለሚተማመኑበት ወገኖች እነዚያን ሁሉ ድንቅ ነገሮች ያደረገ አምላክ ከአንተ በቀር አልተሰማም፤ አልታየም፤ የተረዳም የለም።
ሞአብና ከተሞችዋማ እነሆ ተደምስሰዋል፤ የሚያስደስቱ ወጣቶችዋም ለመታረድ ወርደዋል። እኔ ንጉሡ ይህን ተናግሬአለሁ ስሜም ‘የሠራዊት አምላክ’ ነው።
እንዲሁም እግዚአብሔር ከሞት ያስነሣውን፥ ከሚመጣው ቊጣ የሚያድነንን፥ የልጁን የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት እንዴት እንደምትጠባበቁም ይመሰክራሉ።
እንደ ደመና በዙሪያችን የከበቡን እነዚህ ሁሉ ምስክሮች ስላሉን እኛ እንደ ሸክም የሆነብንን ነገር ሁሉ በእኛ ላይ የተጣበቀብንን ኃጢአት አስወግደን በፊታችንም ያለውን የሩጫ እሽቅድድም በትዕግሥት በመጽናት እንሩጥ።
ሙሴ በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርኩት አሁንም እንደዚያው ብርቱ ነኝ፤ በዚያን ጊዜ ለመዋጋት ለመውጣትና ለመግባት የነበረኝ ጒልበት አሁንም እንደዚያው ነው።
ሴቲቱ በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ የታላቅ ንስር ክንፎች የሚመስሉ ሁለት ክንፎች ተሰጡአት፤ እዚያም ከእባቡ ፊት ርቃ ሦስት ዓመት ተኩል በእንክብካቤ ተይዛ ትጠበቅ ነበር።
የመጀመሪያው እንስሳ አንበሳ ይመስል ነበር፤ ሁለተኛው በሬ ይመስል ነበር፤ ሦስተኛው የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛው የሚበር ንስር ይመስል ነበር።
ከዚህ በኋላ ሶምሶን “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አስበኝ፤ አምላኬ ሆይ! እባክህ ኀይል ስጠኝና ፍልስጥኤማውያን ዐይኖቼን ስላወጡ አንድ ጊዜ ብቻ እንድበቀላቸው አድርገኝ!” ብሎ ጸለየ።