Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 103:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በጐልማሳነቴ ሕይወቴን በመልካም ነገር ሁሉ ይሞላታል፤ እንደ ንስርም ወጣትነቴን ያድሳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጕልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጎልማሳነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ት​ና​ወጥ፥ ምድ​ርን መሠ​ረ​ታት፥ አጸ​ና​ትም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 103:5
12 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ሥጋው እንደገና እንደ ልጅ ሥጋ ሆኖ ይታደሳል፤ እንደ ወጣትነቱም ጊዜ ይመለሳል።


አንተ ምግብ ስትሰጣቸው እነርሱም ይመገባሉ፤ አንተ እጅህን ስትዘረጋ እነርሱም መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ በልተው ይጠግባሉ።


እርሱ የተጠሙትን ያረካቸዋል፤ የተራቡትንም ብዙ መልካም ነገር በመስጠት ያጠግባቸዋል።


በጠላቶቼ ፊት ታላቅ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ትቀባልኛለህ፤ ጽዋዬም እስኪትረፈረፍ ድረስ ይሞላል።


ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ።


አንተ የመረጥካቸውና በተቀደሰ አደባባይህ እንዲኖሩ ወደ ራስህ ያቀረብካቸው፥ ደስ ይበላቸው፤ እኛም ከቤትህ በሚገኘው መልካም ነገርና ከመቅደስህ በሚገኘው በረከት እንረካለን።


በእግዚአብሔር ተማምነው የሚኖሩ ግን ኀይላቸው ይታደስላቸዋል። እንደ ንሥር በክንፍ ይበራሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም።


የቀድሞውን የወይን ተክል እመልስላታለሁ፤ የመከራንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤ እዚያም ከግብጽ ስትወጣ በወጣትነትዋ ወራት በነበራት ሁኔታ በደስታ ትዘምራለች።


ስለዚህ ተስፋ አንቈርጥም፤ ምንም እንኳ የውጪው ሰውነታችን ቢጠፋ የውስጡ ሰውነታችን በየቀኑ ይታደሳል።


የዚህ ዓለም ሀብታሞች እንዳይታበዩ ወይም ተስፋቸውን አስተማማኝ ባልሆነ ሀብት ላይ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፤ እንዲሁም ተስፋቸው እኛን ደስ እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን እዘዛቸው።


ሙሴ በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርኩት አሁንም እንደዚያው ብርቱ ነኝ፤ በዚያን ጊዜ ለመዋጋት ለመውጣትና ለመግባት የነበረኝ ጒልበት አሁንም እንደዚያው ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos