ኢሳይያስ 40:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ የምድርን ክበብ ያጸናል፤ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው፥ እንደ ድንኳንም ለመኖሪያ የሚዘረጋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፥ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥ |
ስለ ግብጽ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል የሚከተለው ነው፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በደመና ሆኖ በፍጥነት ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጻውያን ጣዖቶች በፊቱ ይናወጣሉ፤ የግብጽ ሕዝብም በፍርሃት ይርበደበዳሉ።
“የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ዙፋን የዘረጋ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ የዓለምም መንግሥታት ሁሉ አምላክ አንተ ነህ፤ ሰማይና ምድርን የፈጠርክ አንተ ነህ።
በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቦች እንደ አንድ የውሃ ጠብታ ናቸው፤ በሚዛንም ላይ እንዳለ ዐቧራ ናቸው፤ ደሴቶችም በእርሱ ዘንድ እንደ ትቢያ የቀለሉ ናቸው።
በምድር ላይ ፍትሕን እስኪመሠርት ድረስ እርሱ አይታክትም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ በሩቅ ያሉ ሕዝቦችም የእርሱን ትምህርት ለመስማት ይናፍቃሉ።”
ሰማይን የፈጠረና ከዳር እስከ ዳር የዘረጋው፥ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሠራ፥ ሕይወትንና እስትንፋስንም የሰጣቸው፥ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦
በእናትህ ማሕፀን የፈጠረህ አዳኝህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉን ነገር የፈጠርኩ፥ ሰማያትን ብቻዬን የዘረጋሁ፥ ምድርንም ብቻዬን ያነጠፍኩ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው?
በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን የዐናቅን ዘሮች አይተናል፤ እኛ በእነርሱ ፊት ልክ እንደ ፌንጣ ያኽል ሆነን ነበር የታየነው፤ እነርሱም እንደዚያው አድርገው ሳይመለከቱን አይቀሩም” አሉ።