Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 40:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከቶ ይህን አታውቁምን? አልሰማችሁምን? ከመጀመሪያው ጀምሮ አልተነገራችሁምን? ምድር ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አላወቃችሁምን? አልሰማችሁምን? ከጥንት አልተነገራችሁምን? ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አላወቃችሁም? ወይስ አልሰማችሁ ይሆን? ከጥንትስ አልተወራላችሁም? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁም?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አላ​ወ​ቃ​ች​ሁ​ምን? ወይስ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? ከጥ​ን​ትስ አል​ተ​ወ​ራ​ላ​ች​ሁ​ምን? ወይስ ምድር ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ አላ​ስ​ተ​ዋ​ላ​ች​ሁ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 40:21
17 Referencias Cruzadas  

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።


እግዚአብሔር የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋ፤ ምድርም በባዶ ቦታ እንድትንጠለጠል አደረገ።


የሠሩአቸውና የሚታመኑባቸው ሁሉ እንደነዚህ ጣዖቶች ናቸው።


እግዚአብሔር ብቸኛ ዳኛ ስለ ሆነ ሰማያት የእርሱን ፍትሕ ያውጃሉ።


የዛፍ ቅርንጫፎች በሚደርቁበትም ጊዜ ይሰባበራሉ፤ ሴቶችም ለእሳት ማገዶ ይለቅሙአቸዋል፤ ሕዝቡ ማስተዋል ስለ ጐደለው ፈጣሪ አምላኩ አይራራለትም፤ ምንም ምሕረት አያደርግለትም።


“ከብዙ ጊዜ በፊት ይህን ሁሉ የወሰንኩት እኔ ራሴ መሆኔን አልሰማህምን? ዕቅዱን አውጥቼ አሁን ለፍጻሜ ያደረስኩት እኔ ነኝ፤ የተመሸጉ ከተሞችን የፍርስራሽ ክምር እንድታደርጋቸው ኀይልን የሰጠሁህ እኔ ነኝ።


ከቶ አታውቅምን? ከቶስ አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው፤ ዓለምን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው፤ እርሱ ከቶ አይደክምም ወይም አይታክትም፤ ሐሳቡን መርምሮ ሊደርስበት የሚቻለው የለም።


ተቃጥሎ ዐመድ የሚሆነውን እንጨት እስከ ማምለክ ድረስ ሰው እንዴት ሞኝ ይሆናል? የሞኝነት አስተሳሰቡ አሳስቶታል፤ ራሱን ማዳን አይችልም፤ ወይም “ይህ በቀኝ እጄ ያለው ነገር ጣዖት እንጂ አምላክ አይደለም።” ብሎ መናገር አይችልም።


“እናንተ ዐመፀኞች! በአእምሮአችሁ ያዙት፤ በልባችሁም አኑሩት።


እኔ ምድርን መሠረትኩ፤ ሰማያትንም ዘረጋሁ። ስጠራቸውም ይገኛሉ።


ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?


ይሁን እንጂ እርሱ እንዴት ያለ ቸር አምላክ መሆኑን የሚመሰክር መልካም ሥራ ማድረጉን አላቋረጠም፤ ከሰማይ ዝናብን አዘነበላችሁ፤ የመከር ወራትንም ሰጣችሁ፤ በምግብና በደስታ ልባችሁን አረካ።”


ሰዎች እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ አስነዋሪ ነገር እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos