Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ማንም ሳያግዘው ሰማይን የዘረጋ እርሱ ነው፤ እርሱ በባሕር ሞገድ ላይ ይራመዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርሱ ብቻውን ሰማያትን ዘርግቷል፤ በባሕርም ማዕበል ላይ ይራመዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሰማ​ያ​ትን ብቻ​ውን ይዘ​ረ​ጋል፥ በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ሄድ በማ​ዕ​በል ላይ ይሄ​ዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 9:8
22 Referencias Cruzadas  

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።


ሌሎች ሕዝቦች የሚሰግዱላቸው አማልክት ጣዖቶች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን የፈጠረ አምላክ ነው።


በእስትንፋሱ ሰማይን ያጠራል፤ በእጁም ተወርዋሪውን እባብ ይወጋል።


እግዚአብሔር የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋ፤ ምድርም በባዶ ቦታ እንድትንጠለጠል አደረገ።


እግዚአብሔር ሰማይን እንደ ቀለጠ መስተዋት ቢዘረጋ፥ አንተ በአጠገቡ ሆነህ ትረዳዋለህን?


እስከዚህ ድረስ ትመጣለህ! ከዚህም አታልፍም! የአንተም ብርቱ ማዕበል እዚህ ይቁም! ያልኩ እኔ ነኝ።


“ወደ ባሕሩ ጥልቀት ወርደሃልን? በውቅያኖስ ወለል ላይ ተመላልሰህ ታውቃለህን?


እግዚአብሔር ሰማያትን በቃሉ፥ በሰማይ የሚገኙትን ፍጥረቶች በትእዛዙ ፈጠረ።


መንገድህ በባሕር መካከል ነበር፤ ያለፍከውም በታላላቅ ወንዞች በኩል ነበር፤ ነገር ግን የእግርህ ዱካ አልተገኘም።


እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።


ሰማይን የፈጠረና ከዳር እስከ ዳር የዘረጋው፥ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሠራ፥ ሕይወትንና እስትንፋስንም የሰጣቸው፥ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦


በእናትህ ማሕፀን የፈጠረህ አዳኝህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉን ነገር የፈጠርኩ፥ ሰማያትን ብቻዬን የዘረጋሁ፥ ምድርንም ብቻዬን ያነጠፍኩ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?


“ጣዖቶች ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ መሆናቸውንና አንተ እግዚአብሔር ጣዖቶችን ሁሉ እንደምትደመስስ ንገራቸው” አልከኝ።


እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን ሠራ፤ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤


እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን፥ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤


ሰማይን የዘረጋ፥ ምድርን የመሠረተ፥ ለሰውም የሕይወትን እስትንፋስ የሰጠ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል እንዲህ ይላል፦


ደቀ መዛሙርቱ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያኽል እየቀዘፉ ከተጓዙ በኋላ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos