ኢሳይያስ 19:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ስለ ግብጽ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል የሚከተለው ነው፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በደመና ሆኖ በፍጥነት ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጻውያን ጣዖቶች በፊቱ ይናወጣሉ፤ የግብጽ ሕዝብም በፍርሃት ይርበደበዳሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ስለ ግብጽ የተነገረ ንግር፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጻውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ስለ ግብፅ የተነገረ ራእይ። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅም የእጆቻቸው ሥራዎች በፊቱ ይዋረዳሉ፤ የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፥ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብፅም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል። Ver Capítulo |
ከጽዋው መጠጣት የሚገባቸው ሌሎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የግብጽ ንጉሥ ከባለሟሎቹና ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር፥ የግብጽ ሕዝብና በግብጽ የሚኖሩ መጻተኞች ሁሉ፥ በዑፅ ምድር የሚኖሩ ነገሥታት ሁሉ፥ በፍልስጥኤማውያን ከተሞች፥ በአስቀሎና፥ በጋዛ፥ በዔቅሮንና በአሽዶድ፥ በሌሎች ቦታዎችም የሚኖሩ የኤዶም፥ የሞአብና የዐሞን ሕዝቦች ሁሉ፥ የጢሮስና የሲዶና ነገሥታት ሁሉ፥ በሜዲትራኒያን ባሕር ዙሪያ በሚገኙ አገሮች ያሉ ነገሥታት ሁሉ፥ የደዳን፥ የቴማና የቡዝ ከተሞች ሁሉ፥ የግንባራቸውን ግራና ቀኝ ጠጒር የሚላጩ ሕዝቦች ሁሉ፥ የዐረብ አገር ነገሥታት ሁሉ፥ በበረሓ የሚኖሩ ነገዶች ነገሥታት ሁሉ፥ የዘምሪ፥ የዔላምና የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፥ ሌሎችም በስተሰሜን በኩል በሩቅና በቅርብ ያሉ ነገሥታት ሁሉ በየተራቸው። በምድር ላይ የሚኖሩት ሕዝብ ሁሉ፥ ከዚህ ጽዋ ይጠጣሉ፤ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ከዚህ ጽዋ መጠጣት ይኖርበታል።