ኢሳይያስ 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ ሁሉ ሞተዋል፤ ዳግመኛም በሕይወት አይኖሩም፤ አንተም ቀጥተሃቸው ስለ ተደመሰሱ፥ ዳግመኛ አይነሡም፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ሞተዋል፤ ከእንግዲህ በሕይወት አይኖሩም፤ መንፈሳቸው ተነሥቶ አይመጣም። አንተ ቀጣሃቸው፤ አጠፋሃቸው፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ደመሰስህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፤ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፤ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ እንዳልነበር አድርገሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሙታን ሕይወትን አያዩአትም፤ ባለ መድኀኒቶችም አያስነሡም፤ ስለዚህም አንተ አምጥተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ ወንዶቻቸውንም ሁሉ አስወግደሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፥ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፥ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል አጥፍተሃቸውማል፥ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ምን ምን አድርገሃል። |
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ በፔዖር የነበረውን ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ጣዖት አመለኩ፤ ሕይወት ለሌላቸው አማልክት የቀረበውንም የመሥዋዕት ሥጋ በሉ።
በዚህ ሁሉ የግፍ ሥራችሁ እግዚአብሔር እናንተን በሚቀጣበት ጊዜ ምን ታደርጉ ይሆን? በእናንተ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ከሩቅ አገር በሚያመጣበት ጊዜስ ምን ይበጃችሁ ይሆን? ርዳታስ ለማግኘት የምትሄዱት ወደማን ነው? ሀብታችሁንስ የት ትሸሽጉታላችሁ?
ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።
የሠራዊት ጌታ አምላክ ነጐድጓድን፥ የመሬት መናወጥን፥ ታላቅ ድምፅን፥ ዐውሎ ነፋስን፥ ሞገድንና የሚባላ የእሳት ነበልባልን በጠላቶችሽ ላይ በመላክ አንቺን ይታደግሻል።
“በመንተባተብ የሚቀባጥሩትን ሟርተኞችንና የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ” እያሉ የሚሰብኩአችሁ ወገኖች አሉ፤ ታዲያ፥ ስለ ሕያዋን ሙታንን ከመጠየቅ ይልቅ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን?
እዚያም፥ ለማየት፥ ለመስማት፥ ለመብላትና ለማሽተት የማይችሉትንና ከእንጨትና ከድንጋይ በሰው እጅ የተሠሩትን ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ።