የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቈስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።”
ኢሳይያስ 20:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢትዮጵያ የሚተማመኑና በግብጽም የሚመኩ ሁሉ ግራ ተጋብተው ተስፋ ይቈርጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢትዮጵያ ተስፋ ያደረጉ፣ በግብጽ የተመኩ ይፈራሉ፤ ይዋረዳሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ፤ ያፍራሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግብፃውያን ከኢትዮጵያውያን ጋር ይሸነፋሉ፤ ግብፃውያንም ከታመኑባቸው ጋር ይፈራሉ፤ ያፍሩማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል። |
የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቈስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።”
ብዙ ፈረሶች፥ ሠረገሎችና ወታደሮች ባሉት ብርቱ በሆነው በግብጽ ሠራዊት ተማምነው ርዳታ ለማግኘት ወደ ግብጽ ለሚወርዱ ወዮላቸው! ነገር ግን የእስራኤልን ቅዱስ ርዳታ አይለምኑም፤ መመሪያውንም አይቀበሉም።
ምንአልባት ግብጽ ትረዳኛለች ብለህ ተስፋ አድርገህ ይሆናል፤ ነገር ግን በእርስዋ መታመን በሸምበቆ የመደገፍ ያኽል መሆኑን ዕወቀው፤ ተሰንጥሮ እጅህን ከሚወጋው በቀር ሸምበቆ ለምንም አይጠቅምህም፤ በግብጽ ንጉሥ የሚተማመንም የሚገጥመው ዕድል ይህንኑ የመሰለ ነው።’ ”
አንተ ከአሦራውያን ባለሥልጣኖች የመጨረሻውን ዝቅተኛ መኰንን እንኳ ለመቋቋም የምትችል አይደለህም፤ ይህም ሆኖ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ይልኩልኛል ብለህ ተስፋ ታደርጋለህ።
በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ የአሦር ንጉሥ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኛ እጅ ላከ፦
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ግብጽን፥ አማልክትዋንና ነገሥታቶችዋን፥ የቴብስ አምላክ የሆነውን አሞንን፥ የግብጽን ንጉሥና በእርሱ የሚተማመኑትን ሁሉ እቀጣለሁ።
ይልቁንስ እስራኤል ለእርዳታ ወደ ግብጽ በመሄድ የበደለችውን በደል ታስታውስበታለች እንጂ ርዳታ ለማግኘት ዳግመኛ በእነርሱ ላይ አትተማመንም። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”