ኢሳይያስ 10:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የድኾች መብት እንዳይከበርና የተበደሉ ፍትሕ እንዳያገኙ የምታደርጉበት ዘዴ ይኸው ነው፤ በዚሁ ዘዴ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና አሳዳጊ የሌላቸውን የሙት ልጆች ንብረት ትነጥቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የድኾችን መብት ለሚገፍፉ፣ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የድኾችን መብት ለሚገፉ፤ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፤ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፤ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መበለቶች ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ የሙት ልጆችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሃውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ ወዮላቸው! |
መልካም ማድረግንም ተማሩ፤ ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ የተጨቈኑትን ታደጉ፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት ጠብቁ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ ስሙ።”
መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።
ሰውን በነገር ወንጀለኛ የሚያደርጉ፥ ተከሳሽንም በፍርድ ሸንጎ የሚያጠምዱ፥ በሐሰተኛ ምስክር ንጹሕ ሰው ፍትሕ እንዳያገኝ በሐሰት የሚመሰክሩትን ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል።
ስለዚህ የሕዝቡን መሪዎችና አማካሪዎች ወደ ፍርድ አቅርቦ እንዲህ ይላቸዋል፦ “የወይኑን አትክልት ቦታ ዘረፋችሁ፤ ከድኾች በተዘረፈው ሀብትም ቤታችሁን ሞላችሁ።
ሞኞች የሞኝነትን ንግግር ይናገራሉ፤ አእምሮአቸውም በደልን ያሤራል፤ ስለ እግዚአብሔር ስሕተተኛ ንግግርን በማሠራጨት ክሕደትን ያስፋፋል። የተራቡትን አያጠግቡም።
ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።
መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አትበዝብዙ፤ በዚህች ምድር የሚኖሩ ንጹሓን የሆኑ ሰዎችን በግፍ አትግደሉ፤ እንዳትጠፉም ለሐሰተኞች አማልክት አትስገዱ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ንጹሓንን በብር፥ ድኾችን በጫማ ይሸጡ ነበር።
ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በትቢያ ላይ ጥለው ራስ ራሳቸውን ይረግጣሉ፤ የተዋረዱ ምስኪኖችንም ገፍትረው ከመንገድ ያስወጣሉ፤ አባትና ልጅ ሁለቱም ከአንዲት ሴት ጋር ያመነዝራሉ፤ በዚህም ሥራቸው የተቀደሰውን ስሜን ያረክሳሉ።
ያ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሸሽቶ ሲሄድ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወይም አምልጦ ወደ ቤቱ ሲገባ እጁን በግድግዳ ላይ ቢያሳርፍ እባብ እንደሚነድፈው ሁኔታ ይሆንባችኋል።
ከዚህም በኋላ እንዲህ አልኳቸው፦ “የእስራኤል ሕዝብ ልጆች መሪዎችና የእስራኤል ሕዝብ ገዢዎች! አድምጡ! ትክክለኛ ፍርድን ማወቅ ይገባችሁ አልነበረምን?
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።
“ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገባ፥ በሩን የምትዘጉ እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ!” [