Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 10:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሕዝቤን የሚጨቊን ግፍ የሞላበት ሕግ ለምታወጡ ወዮላችሁ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ ጭቈና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፤ ጭቈና የሞላበትን ሥርዓት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ክፉ​ንም ጽሕ​ፈት ለሚ​ጽፉ ወዮ​ላ​ቸው!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1-2 መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፥ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 10:1
39 Referencias Cruzadas  

“እናንተ የሕግ መምህራን ወዮላችሁ! የዕውቀት በር መክፈቻ የሆነውን የእውነት ቊልፍ ይዛችኋል፤ ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።”


“እናንተ ግብዞች የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! ከአዝሙድ፥ ከእንስላል፥ ከከሙን ዐሥራት ትሰጣላችሁ፤ ነገር ግን በሕግ ውስጥ የሚገኙትን ዋና ዋና ነገሮች ትተዋላችሁ፤ እነርሱም ትክክለኛ ፍርድ፥ ምሕረትና ታማኝነት ናቸው፤ ያንን ሳትተዉ ይህንንም ማድረግ ይገባችሁ ነበር።


የካህናት አለቆችና የዘብ ኀላፊዎች ኢየሱስን ባዩት ጊዜ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስ ግን “እኔ በበኩሌ ምንም በደል አላገኘሁበትም፤ ብትፈልጉ እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት” አላቸው።


ወላጆቹ ይህን ያሉት ኢየሱስን “መሲሕ ነው” የሚል ሰው ቢኖር የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከምኲራብ ሊያስወጡት ተስማምተው ስለ ነበረ እነርሱን በመፍራት ነበር።


ሰው ሁሉ እንደነዚህ ባሉት ሰዎች ላይ በመሳለቂያ እንቆቅልሽ እንዲህ ይላል፦ “ያንተ ያልሆነውን የምታግበሰብስ ወዮልህ! በመያዣነት በተወሰዱ ዕቃ ራስህን የምታበለጽገው እስከ መቼ ነው?”


በአገሪቱ ላይ መኖር የሚገባችሁ እናንተ ብቻ መስሎአችሁ፥ ቀድሞ በነበራችሁ ይዞታ ላይ ለመቀላቀል ሰዎችን ሁሉ እያስወጣችሁ ቤትን ከቤት ማያያዝና እርሻንም በእርሻ ላይ ለመቀላቀል ለምትፈልጉ ወዮላችሁ!


በቃየል መንገድ ስለ ሄዱ፥ ለገንዘብ ብለው በበለዓም ስሕተት ስለ ወደቁ፥ ቆሬም እንደ ተቃወመ በመቃወማቸው ስለ ጠፉ ወዮላቸው!


የሰው ልጅ ስለ እርሱ በተጻፈው መሠረት ይሞታል፤ ነገር ግን የሰው ልጅን አሳልፎ ለሚሰጥ ለዚያ ሰው ወዮለት! ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር።”


“እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! የነቢያትን መቃብር ትገነባላችሁ፤ የጻድቃንንም ሐውልት ታስጌጣላችሁ።


“እናንተ ግብዞች የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! በውስጣቸው በሞቱ ሰዎች አጥንትና በርኩስ ነገር ሁሉ የተሞሉ፥ በውጪ ግን በኖራ ተለስነው የሚያምሩ መቃብሮችን ትመስላላችሁ።


ሰውን በመግደል ከተማን ለምትቈረቊሩና፥ በበደል ዋና ከተማን ለምትሠሩ ወዮላችሁ!


አደጋ እንዳይደርስበት መኖሪያውን ከፍ ባለ አምባ ላይ የሚመሠርትና በሕገ ወጥ ገቢ ቤቱን ለሚሠራ ወዮለት!


ይህ ሁሉ የሚደርስባችሁ የንጉሥ ዖምሪን ሥርዓት ስለ ጠበቃችሁና የንጉሥ አክዓብን አካሄድ ሁሉ ስለ ተከተላችሁ ነው፤ በእነርሱ ባህል ስለ ተመራችሁ አጠፋችኋለሁ፤ የከተማይቱን ነዋሪዎችም የሰው ሁሉ መሳቂያ አደርጋቸዋለሁ፤ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ እንድትሸከሙ አደርጋችኋለሁ።”


“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት፥ በጢሮስና በሲዶና ከተሞች ተደርገው ቢሆን ኖሮ በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የሐዘን ልብስ ለብሰውና ዐመድ በላያቸው ላይ ነስንሰው ገና ዱሮ ንስሓ በገቡ ነበር!


ከእንጨት ተጠርቦ የተሠራውን ነገር “ንቃ!” ከድንጋይ ተቀርጾ የተሠራውንም ነገር “ተነሥ!” ለምትል ለአንተ ወዮልህ! ለመሆኑ ጣዖት አንዳች ምሥጢር ሊገልጥልህ ይችላልን? እነሆ ጣዖት በብርና በወርቅ ተለብጦ የተሠራ ነው፤ የሕይወት እስትንፋስ ግን ፈጽሞ የለውም።


ኀፍረተ ሥጋው ሲገለጥ ለማየት ለሰው ቊጣህን እንደ ጠንካራ መጠጥ የምትሰጥና እስኪሰክርም ድረስ የምታጠጣው አንተ ሰው ወዮልህ!


ቤቱን በግፍ ሰገነቱንም በዐመፅ ለሠራተኞች የድካማቸውን ዋጋ ሳይከፍል ለሚያሠራ ሰው ወዮለት!


በማታለል ገመድ ኃጢአትን፥ በሠረገላ ገመድ ተንኰልን ለሚጐትቱ ወዮላቸው!


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


አይደለም! በልባችሁ ክፉ ነገርን ታቅዳላችሁ፤ በምድር ላይ የምትፈጽሙትም ሁሉ የዐመፅ ሥራ ነው።


ጠጥተው ለመስከር ማልደው ወደ መሸታ ቤት ለሚገሠግሡ፥ የወይን ጠጅ እስኪያቃጥላቸው ሌሊቱንም ሁሉ በዚያው መቈየት ለሚፈልጉ ወዮላቸው!


ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል” ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።


ስለዚህ የሕዝቡን መሪዎችና አማካሪዎች ወደ ፍርድ አቅርቦ እንዲህ ይላቸዋል፦ “የወይኑን አትክልት ቦታ ዘረፋችሁ፤ ከድኾች በተዘረፈው ሀብትም ቤታችሁን ሞላችሁ።


ጉቦ ተቀብለው በደል የሠራውን ሰው ነጻ በመልቀቅ፥ በደል የደረሰበትን ሰው ፍትሕ ለሚነፍጉ ወዮላቸው!


ሰውን በነገር ወንጀለኛ የሚያደርጉ፥ ተከሳሽንም በፍርድ ሸንጎ የሚያጠምዱ፥ በሐሰተኛ ምስክር ንጹሕ ሰው ፍትሕ እንዳያገኝ በሐሰት የሚመሰክሩትን ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል።


ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።


በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት በማጓደል ዐምፀናል፤ አምላካችንን ትተን ወደ ኋላ አፈግፍገናል፤ በልባችን ውስጥ ውሸትን አውጠንጥነን ስም በማጥፋትና በከሐዲነት ገልጠናቸዋል።


ድኻ ለፍርድ ቢቀርብ ድኽነቱን በማየት አድልዎ አታድርግለት።


“በፍርድ አደባባይ አድልዎ በማድረግ የድኻውን ፍርድ አታጣምበት፤


ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በትቢያ ላይ ጥለው ራስ ራሳቸውን ይረግጣሉ፤ የተዋረዱ ምስኪኖችንም ገፍትረው ከመንገድ ያስወጣሉ፤ አባትና ልጅ ሁለቱም ከአንዲት ሴት ጋር ያመነዝራሉ፤ በዚህም ሥራቸው የተቀደሰውን ስሜን ያረክሳሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios