ዕብራውያን 7:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ መሐላ ምክንያት ኢየሱስ ለተሻለው ቃል ኪዳን ዋስ ሆኖአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ መሐላ የተነሣ፣ ኢየሱስ ለተሻለ ኪዳን ዋስ ሆኗል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ መሐላ ምክንያት ኢየሱስ ለተሻለው ቃል ኪዳን ዋስ ሆኖአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስ ይህን ያህል በምትበልጥና ከፍ ባለች ሹመት ተሾመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል። |
ከዚህም በላይ ስለ ልጁ ደኅንነት ራሴን ዋስ አድርጌ ለአባቴ ሰጥቼአለሁ፤ ደግሞም ‘ልጁን በደኅና መልሼ ባላመጣው በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ተወቃሽ ልሁን’ ብዬ ቃል ገብቼለታለሁ።
እንደ ሽመላ እጮኽ ነበር፤ እንደ ርግብ የሐዘን ድምፅ አሰማ ነበር፤ ወደ ሰማይም አሻቅቤ ከመመልከቴ የተነሣ፥ ዐይኖቼ በጣም ደክመው ነበር። ጌታ ሆይ! እባክህን ከዚህ ሁሉ መከራ አድነኝ!
ያም መሪ ለአንድ ሳምንት ከብዙ ሕዝቦች ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ በሳምንቱም እኩሌታ መሥዋዕቱንና ቊርባኑን ያስቀራል፤ በእነርሱም ፈንታ ጥፋት የሚያስከትለው ርኲሰት እንዲተካ ያደርጋል። ይህም የሚሆነው በዚያ አጥፊ መሪ ላይ የታወጀው ቅጣት እስኪፈጸም ድረስ ነው።”
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።
እንግዲህ “አዲስ ቃል ኪዳን” ሲል የፊተኛውን ቃል ኪዳን አሮጌ አድርጎታል ማለት ነው፤ ስለዚህ የተሠራበትና አሮጌው ነገር ሁሉ የሚጠፋበት ጊዜ ተቃርቧል።