ዕብራውያን 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ ያንን ትውልድ ተቈጥቼ፥ ‘ልባቸው ዘወትር ይሳሳታል፤ መንገዴንም አላወቁም’ አልኩ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤ እንዲህም አልሁ፤ ‘በልባቸው ዘወትር ይስታሉ፤ መንገዴንም አላወቁም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአርባ ዓመታት፤ ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ “ዘወትር በልባቸው ይስታሉ፤ መንገዴን ግን አላወቁም፤” አልኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ይህቺን ትውልድ ተቈጣኋት፤ እንዲህም አልሁ፦ ‘ልባቸው ዘወትር ይስታል፤ እነርሱ ግን መንገዴን አላወቁም።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ፦ ዘወትር በልባቸው ይስታሉ መንገዴን ግን አላወቁም አልሁ፤ |
እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።
ነቢያቱና ካህናቱ እንኳ ሰክረው ይንገዳገዳሉ፤ ብዙ ወይን ጠጅና የሚያሰክርም ጠንካራ መጠጥ ስለ ጠጡ አእምሮአቸው ታውኮ ይሰናከላሉ፤ ነቢያቱ ሰክረው ከመደናበራቸው የተነሣ እግዚአብሔር የገለጠላቸውን ራእይ አያስተውሉም፤ ካህናቱም እጅግ ስለሚሰክሩ ለሚቀርብላቸው ጉዳይ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት አይችሉም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”
ስለዚህ ከእንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቁታል፤ የጥንቈላ ዘንጋቸውም ለጥያቄአቸው መልስ የሚሰጥ ይመስላቸዋል፤ በዝሙት መንፈስም ተመርተው ከእግዚአብሔር ርቀዋል።
ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።
ነገር ግን የእኔ ሐሰተኛነት የእግዚአብሔርን እውነት በመግለጥ፥ የክብሩን ብዛት የሚያሳይ ከሆነ ታዲያ፥ እኔ እንደ ኃጢአተኛ የሚፈረድብኝ ስለ ምንድን ነው?