Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለአርባ ዓመታት፤ ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ “ዘወትር በልባቸው ይስታሉ፤ መንገዴን ግን አላወቁም፤” አልኩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤ እንዲህም አልሁ፤ ‘በልባቸው ዘወትር ይስታሉ፤ መንገዴንም አላወቁም።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ስለዚህ ያንን ትውልድ ተቈጥቼ፥ ‘ልባቸው ዘወትር ይሳሳታል፤ መንገዴንም አላወቁም’ አልኩ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ስለ​ዚህ ይህ​ቺን ትው​ልድ ተቈ​ጣ​ኋት፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦ ‘ልባ​ቸው ዘወ​ትር ይስ​ታል፤ እነ​ርሱ ግን መን​ገ​ዴን አላ​ወ​ቁም።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ፦ ዘወትር በልባቸው ይስታሉ መንገዴን ግን አላወቁም አልሁ፤

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 3:10
20 Referencias Cruzadas  

ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተጸየፍኳት፦ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ “እነርሱም መንገዴን አላወቁም” አልሁ።


ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።


“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”


እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ዐመፀኛና የሚያስመርር ትውልድ፥ ልቡን ያላቀና ትውልድ፥ መንፈሱም በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነ።


እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፥


የዝሙት መንፈስ አስቶአቸዋልና፥ እነርሱም ከአምላካቸው ርቀው አመንዝረዋልና ሕዝቤ ግዑዝ እንጨታቸውን ይጠይቃሉ፥ በትራቸውም ይመልስላቸዋል።


እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ጠላታቸው ሆነ፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።


ወንድሞች ሆይ! ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤


እኔ ግን እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም።


ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ፥ ዙሪያውን በቁጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። እርሱም ዘረጋ፤ እጁም ዳነች።


እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይቀባዥራሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ።


ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። ሃሌ ሉያ።


ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ ጌታንም አመለኩ፤ እርሱም የእስራኤልን መከራ ሊታገሠው የማይቻለው ሆነ።


ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነተኛነት በእኔ ውሸት ለክብሩ ከሞላ፥ ለምን እኔ እስካሁን እንደ ኃጢአተኛ ይፈረድብኛል?


በምድረ በዳ ምን ያህል አስቈጡት፥ በበረሃም አሳዘኑት።


ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩም ጌታ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።


እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ እግዚአብሔር ተገቢ ያልሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤


ዐሥሩም ይህንን በሰሙ ጊዜ በሁለቱም ወንድማማቾች ተቆጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios