ይህም የሚከማቸው እህል በግብጽ ምድር ላይ ወደፊት በሚመጡት ሰባት የራብ ዓመቶች ለአገሪቱ መጠባበቂያ ይሆናል፤ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ በራብ ከመጐዳት ትድናለች።”
ዘፍጥረት 47:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ራቡ እየጸና ስለ ሄደ፥ ከየትም አገር እህል ለማግኘት አልተቻለም ነበር፤ የግብጽና የከነዓን ሕዝቦችም በረሀቡ እጅግ ተጐድተው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመላው ምድር እህል ባለመኖሩ ራቡ እየጸና ሄደ፤ ከዚህ የተነሣም ግብጽና ከነዓን በራብ እጅግ ተጐዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራብም እጅግ ጸንቶአልና፥ በምድር ሁሉ እህል አልነበረም፥ ከራብም የተነሣ የግብጽ ምድርና የከነዓን ምድር ተጎዳ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርም ሁሉ እህል አልነበረም፤ ራብ እጅግ ጸንቶአልና፤ ከራብም የተነሣ የግብፅ ምድርና የከነዓን ምድር ተጐዳ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርም ሁሉ እህል አልነበረም ራብ እጅግ ጸንቶአልና ከራብም የተነሣ የግብፅ ምድርና የከነዓን ምድር ተጎዳ። |
ይህም የሚከማቸው እህል በግብጽ ምድር ላይ ወደፊት በሚመጡት ሰባት የራብ ዓመቶች ለአገሪቱ መጠባበቂያ ይሆናል፤ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ በራብ ከመጐዳት ትድናለች።”
አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ምድሪቱ ማንም ሊዘዋወርባት የማይችል ደረቅ በረሓና ጠፍ መሆንዋ ስለ ምንድን ነው? ይህንንስ የሚያስተውል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? ለሌሎች ማስረዳት ይችል ዘንድ የገለጥክለትስ ማን ነው?”