Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 47:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በመላው ምድር እህል ባለመኖሩ ራቡ እየጸና ሄደ፤ ከዚህ የተነሣም ግብጽና ከነዓን በራብ እጅግ ተጐዱ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ራብም እጅግ ጸንቶአልና፥ በምድር ሁሉ እህል አልነበረም፥ ከራብም የተነሣ የግብጽ ምድርና የከነዓን ምድር ተጎዳ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ይሁን እንጂ ራቡ እየጸና ስለ ሄደ፥ ከየትም አገር እህል ለማግኘት አልተቻለም ነበር፤ የግብጽና የከነዓን ሕዝቦችም በረሀቡ እጅግ ተጐድተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በም​ድ​ርም ሁሉ እህል አል​ነ​በ​ረም፤ ራብ እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ ከራ​ብም የተ​ነሣ የግ​ብፅ ምድ​ርና የከ​ነ​ዓን ምድር ተጐዳ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በምድርም ሁሉ እህል አልነበረም ራብ እጅግ ጸንቶአልና ከራብም የተነሣ የግብፅ ምድርና የከነዓን ምድር ተጎዳ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 47:13
9 Referencias Cruzadas  

የሚከማቸው እህል፣ ወደ ፊት በግብጽ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።”


አክዓብም አብድዩን፣ “ተነሣና በአገሪቱ ውስጥ ወዳሉት ምንጮችና ሸለቆዎች ሂድ፤ ፈረሶቻችንና በቅሎዎቻችን እንዳይሞቱ በሕይወት እንዲቈዩ ምናልባት ሣር እናገኝ ይሆናል።” አለው።


ይህን መረዳት የሚችል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? እግዚአብሔር ገልጾለት ይህንስ ማስረዳት የሚችል ማን ነው? ምድሪቱስ ሰው እንደማያልፍበት በረሓ ለምን ጠፋች? ለምን ወና ሆነች?


በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣ በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣ በራብ ደርቀው ያልቃሉ።


“በዚያ ጊዜም በግብጽና በከነዓን አገር ሁሉ ታላቅ መከራን ያስከተለ ራብ መጣ፤ አባቶቻችንም የሚበሉትን ዐጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos