ዘፍጥረት 47:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ፈርዖንን ባረከውና ተሰናብቶት ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ያዕቆብ ፈርዖንን መርቆ፣ ተሰናብቶት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንን ባርኮም ያዕቆብ ከፈርዖንም ፊት ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው፤ ከፈርዖንም ፊት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው ከፈርዖንም ፊት ወጣ። |
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱና ወንድሞቹ በግብጽ ምድር እንዲቀመጡ አደረገ፤ ፈርዖን ባዘዘው መሠረት በግብጽ ምድር ምርጥ የሆነውን፥ በራምሴ ከተማ አጠገብ ያለውን ቦታ በይዞታ ሰጣቸው።
ስለዚህም ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ድል በመንሣቱ ሰላምታና የደስታ መግለጫ ያቀርብለት ዘንድ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ ቀደም ሲልም ቶዒ በሀዳድዔዜር ላይ ጦርነት ሲያካሄድ የነበረ ነው፤ ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ለዳዊት ይዞለት ሄደ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቦዔዝ ራሱ ከቤተልሔም ተነሥቶ ወደ እርሻው መጣ፤ አጫጆቹንም “እንደምን ዋላችሁ! እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!” አላቸው። እነርሱም “እግዚአብሔር አንተንም ይባርክህ!” አሉት።