እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”
ዘፍጥረት 43:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወደ እዚህ ያመጡን በመጀመሪያ ጊዜ በስልቻዎቻችን ውስጥ ተመልሶ ስለ ተገኘው ገንዘብ ሳይሆን አይቀርም” በማለት፤ ሰዎቹ ወደ ዮሴፍ ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ “በዚህ ምክንያት ያሠቃዩናል፤ አህዮቻችንን ወስደው እኛንም የእነርሱ ባሪያዎች ያደርጉናል” ብለውም አሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ወደዚህ የመጣነው፣ ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውየው ጥቃት ሊፈጽምብን፣ አስገድዶ ባሮቹ ሊያደርገንና አህዮቻችንን ሊቀማን ይፈልጋል” ብለው ሠጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፥ “ወደዚህ የመጣነው፥ ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውዬው ጥቃት ሊፈጽምብን፥ አስገድዶ ባሮቹ ሊያደርገንና አህዮቻችንን ሊቀማን ይፈልጋል” ብለው ሠጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም ሰዎች ወደ ዮሴፍ ቤት እንደ ገቡ በአዩ ጊዜ እንዲህ አሉ፥ “በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኰሉብን፥ ሊወድቁብንም፥ እኛንም በባርነት ሊገዙን፥ አህዮቻችንንም ሊወስዱ ወደዚህ አስገቡን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ወደ ዮሴፍ ቤት ስለ ገቡ ፈሩ እንዲህም አሉ፦ በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኮልብን ሊወድቅብንም እኛንም በባርነት ሊገዛ አህዮቻችንንም ሊወስድ ወደዚህ አስገባን። |
እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”
በመንገድ ላይ ሳሉ ለዐዳር በሰፈሩበት ቦታ ከእነርሱ አንዱ ለአህያው ጥሬ ለመስጠት ስልቻውን በፈታ ጊዜ በስልቻው አፍ ላይ ገንዘቡ ተቋጥሮ አገኘው።
እርሱም ለወንድሞቹ “ገንዘቤ ተመልሶልኛል፤ ይኸው በስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት!” ብሎ ነገራቸው። ሁሉም በፍርሃት ተንቀጥቅጠው “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ።
ከዚህ በኋላ እህላቸውን ከስልቾቻቸው ባራገፉ ጊዜ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ገንዘባቸውን እንደ ተቋጠረ አገኙ፤ እነርሱና አባታቸው የተመለሰውን ገንዘብ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ።
ከአሁን ቀደም በየስልቻችን ያገኘነውን ገንዘብ እንኳ ከከነዓን መልሰን እንዳመጣንልህ ታውቃለህ፤ ታዲያ አሁን ከጌታህ ቤት ብርም ሆነ ወርቅ የምንሰርቀው ለምንድን ነው?
ሶርያ ከእስራኤል መንግሥት ጋር በመተባበር የጦር ቃል ኪዳን መግባትዋን የይሁዳ ንጉሥ በሰማ ጊዜ እርሱና ሕዝቡ ደንግጠው ልባቸው በነፋስ እንደ ተመታ ዛፍ ተናወጠ።
ከዚህ በኋላ ሌሎቹ አገረ ገዢዎችና ባለ ሥልጣኖች በዳንኤልና በሚያከናውነው የመንግሥት ሥራ ላይ ክስ ለመመሥረት የሚያስችላቸውን ወንጀል ለማግኘት ፈለጉ፤ ነገር ግን ዳንኤል እጅግ ጠንቃቃና ታማኝ ስለ ነበር ምንም ዐይነት ስሕተት ወይም በደል ሊያገኙበት አልቻሉም።
የልጅህን ድንግልና የሚያመለክት ማስረጃ አላገኘሁም ብሎ የልጄን ስም አጐደፈ፤ ለልጄ የድንግልናዋ ማረጋገጫ ምልክት ይኸውና!’ በማለት በመሪዎቹ ፊት የማስረጃውን ሻሽ ይዘርጋ።
ሶምሶን ይህን እንዲያደርግ የሚመራው እግዚአብሔር እንደ ሆነ ወላጆቹ አላወቁም፤ በዚያም ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ይገዙ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንን ለመቃወም ምክንያት ይፈልግ ነበር።