Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 44:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከአሁን ቀደም በየስልቻችን ያገኘነውን ገንዘብ እንኳ ከከነዓን መልሰን እንዳመጣንልህ ታውቃለህ፤ ታዲያ አሁን ከጌታህ ቤት ብርም ሆነ ወርቅ የምንሰርቀው ለምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚህ ቀደምም በየስልቾቻችን አፍ የተገኘውን ብር ከከነዓን እንኳ መልሰን አምጥተናል፤ ታዲያ አሁን ብር ወይም ወርቅ ከጌታህ ቤት እንዴት እንሰርቃለን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከዚህ ቀደምም በየስልቾቻችን አፍ የተገኘውን ብር ከከነዓን እንኳ መልሰን አምጥተናል፤ ታዲያ አሁን ብር ወይም ወርቅ ከጌታህ ቤት እንዴት እንሰርቃለን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ችን አፍ ያገ​ኘ​ነ​ውን ብር እን​ኳን ይዘን ከከ​ነ​ዓን ሀገር ወደ አንተ ተመ​ል​ሰ​ናል፤ ከጌ​ታ​ህስ ቤት ወርቅ ወይስ ብር እን​ዴት እን​ሰ​ር​ቃ​ለን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነሆ በዓይበታችን አፍ ያገኘነውን ብር ይዘን ከከነዓን አገር ወደ አንተ ተመልሰናል ከጌታህ ቤት ወርቅ ወይስ በር እንዴት እንሰርቃለን?

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 44:8
12 Referencias Cruzadas  

እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”


በመንገድ ላይ ሳሉ ለዐዳር በሰፈሩበት ቦታ ከእነርሱ አንዱ ለአህያው ጥሬ ለመስጠት ስልቻውን በፈታ ጊዜ በስልቻው አፍ ላይ ገንዘቡ ተቋጥሮ አገኘው።


ከዚህ በኋላ እህላቸውን ከስልቾቻቸው ባራገፉ ጊዜ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ገንዘባቸውን እንደ ተቋጠረ አገኙ፤ እነርሱና አባታቸው የተመለሰውን ገንዘብ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ።


ከዚህ በፊት በየስልቻዎቻችሁ ጫፍ ተመልሶ የነበረው ገንዘብ በስሕተት ሊሆን ስለሚችል እጥፍ ገንዘብ ይዛችሁ ሂዱ።


“ወደ እዚህ ያመጡን በመጀመሪያ ጊዜ በስልቻዎቻችን ውስጥ ተመልሶ ስለ ተገኘው ገንዘብ ሳይሆን አይቀርም” በማለት፤ ሰዎቹ ወደ ዮሴፍ ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ “በዚህ ምክንያት ያሠቃዩናል፤ አህዮቻችንን ወስደው እኛንም የእነርሱ ባሪያዎች ያደርጉናል” ብለውም አሰቡ።


እነርሱም እንዲህ በማለት መልስ ሰጡት፤ “ጌታችን ሆይ፤ እንዴት እንዲህ ትናገራለህ? እኛ ይህን የመሰለ ነገር እንዳላደረግን በመሐላ እናረጋግጣለን፤


ሰውየውም “የትኞቹን ትእዛዞች?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤


“አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ የሌላ ሰው የሆነውን ማናቸውንም ነገር አትመኝ” የሚሉት ትእዛዞችና ሌሎችም ትእዛዞች ሁሉ “ሰውን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በአንዱ ትእዛዝ ተጠቃለው ይገኛሉ።


“ ‘አትስረቅ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos