Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 14:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሶምሶን ይህን እንዲያደርግ የሚመራው እግዚአብሔር እንደ ሆነ ወላጆቹ አላወቁም፤ በዚያም ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ይገዙ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንን ለመቃወም ምክንያት ይፈልግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዚያ ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፣ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ጠብ እንዲፈጠር እግዚአብሔር ሆነ ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፥ ከፍልስጥአማውያን ጋር ጠብ እንዲፈጠር ጌታ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አባ​ቱና እና​ቱም ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ አላ​ወ​ቁም፤ እርሱ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን ይመ​ልስ ዘንድ ይፈ​ልግ ነበ​ርና። በዚ​ያም ወራት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እስ​ራ​ኤ​ልን ይገዙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን ላይ ምክንያት ይፈልግ ነበርና ነገሩ ከእርሱ ሆነ፥ አባቱና እናቱ ግን አላወቁም። በዚያን ጊዜም ፍልስጥኤማውያን በእስራኤል ላይ ገዦች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 14:4
14 Referencias Cruzadas  

ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት እግዚአብሔር ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።


“ወንድሞቻችሁ በሆኑት በእስራኤላውያን ላይ አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነው በእኔ ፈቃድ ነው” ብሎ እንዲነግር አዘዘው። እነርሱም ሁሉ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች በመሆን ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።


ገና ይህን ተናግሮ ሳይጨርስ ንጉሡ ድንገት ከተፍ ብሎ “ይህን መከራ በእኛ ላይ ያመጣብን እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ እርሱ አንድ ነገር ያደርግ ዘንድ ከዚህ በላይ ምን ልጠብቅ?” አለ።


ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ይኸው ነው።


አካዝያስ ኢዮራምን ሊጠይቅ የሄደው እግዚአብሔር ይህ ጒብኝት የአካዝያስ መጥፊያ እንዲሆን ስለ ፈቀደ ነው፤ አካዝያስ በዚያ በነበረበት ጊዜ እርሱና ኢዮራም የአክዓብን ሥርወ መንግሥት ለማጥፋት እግዚአብሔር የመረጠውን የኒምሺ ልጅ ኢዩን ለመቀበል ወጡ፤


አሜስያስ ግን የዮአስን ምክር ከምንም አልቈጠረውም፥ ይህም የሆነበት ምክንያት አሜስያስ የኤዶማውያንን ጣዖቶች ስላመለከ ድል እንዲሆን እግዚአብሔር ስለ ፈቀደ ነው፤


አምላካችን በሰማይ ነው፤ እርሱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል።


ከዚህ በኋላ ሌሎቹ አገረ ገዢዎችና ባለ ሥልጣኖች በዳንኤልና በሚያከናውነው የመንግሥት ሥራ ላይ ክስ ለመመሥረት የሚያስችላቸውን ወንጀል ለማግኘት ፈለጉ፤ ነገር ግን ዳንኤል እጅግ ጠንቃቃና ታማኝ ስለ ነበር ምንም ዐይነት ስሕተት ወይም በደል ሊያገኙበት አልቻሉም።


ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ለሚልካቸው ለጠላቶችህ አገልጋይ ትሆናለህ። በሁሉ ነገር በመቸገርም ትራባለህ፤ ትጠማለህ፤ ትታረዛለህ። ፈጽሞ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር አንተን በጠላቶችህ እንደ ብረት በጠነከረ የአገዛዝ ቀንበር በብርቱ እንድትጨቈን ያደርጋል።


እነዚህም ሁሉ ከእስራኤላውያን ጋር ጦርነት እንዲገጥሙ እግዚአብሔር ልባቸውን እልኸኛ አድርጎ አነሣሣቸው። ስለዚህም በአጠቃላይ እንዲደመሰሱ ተፈርዶባቸው ያለ ምሕረት ተገደሉ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ ለሙሴ የሰጠው ትእዛዝ ይኸው ነበር።


የእስራኤል ሕዝብ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ ስለዚህም አርባ ዓመት ሙሉ እንዲገዙአቸው እግዚአብሔር ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ሰጣቸው።


ከዚህ በኋላ ሶምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ፤ እዚያም በወይን ተክል ውስጥ አልፈው ሲሄዱ አንድ ደቦል አንበሳ እያገሣ መጣበት፤


ስለዚህም ሦስት ሺህ የሚሆኑ የይሁዳ ሰዎች በዔጣም ወዳለው ዋሻ ሄደው “ፍልስጥኤማውያን ገዢዎቻችን እንደ ሆኑ አታውቅምን? ታዲያ ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው?” ሲሉ ሶምሶንን ጠየቁት። እርሱም “እኔ በእነርሱ ላይ ያደረግኹት ልክ እነርሱ በእኔ ላይ ያደረጉትን ነው” አላቸው።


ሶምሶንም “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ነገር ባደርግ አልወቀስበትም!” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos