ዘፍጥረት 35:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑርህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ ብዛ ተባዛ፤ ሕዝብና የሕዝቦች ማኅበር ከአንተ ይወጣሉ፤ ነገሥታትም ከአብራክህ ይከፈላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፥ ብዛ፥ ተባዛም፥ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጉልበትህ ይወጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለው፥ “አምላክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባዛም፤ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፤ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አለው፦ ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ ብዛ ተባዛም ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ። |
ቀጥሎም እግዚአብሔር አብራምን ወደ ውጪ አወጣውና “ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከዋክብትን መቊጠር ትችል እንደሆን ሞክር፤ እንግዲህ የአንተም ዘሮች እንደዚህ ይበዛሉ” አለው።
አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤
እርስዋን እባርካታለሁ፤ ከእርስዋም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካታለሁ፤ የብዙ ሕዝቦችም እናት ትሆናለች፤ ከዘርዋም መካከል ነገሥታት የሚሆኑ ይገኛሉ።”
ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።
ብንያምንና ሌላውንም ወንድማችሁን መልሶ እንዲሰጣችሁ ሁሉን የሚችል አምላክ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እኔ በበኩሌ ልጆቼን ካጣሁ፥ ባዶ እጄን መቅረቴ ነው።”
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብጽ ለመሄድ አትፍራ፤ እኔ ዘርህን በግብጽ አገር ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ፤
ሁሉን የምችል አምላክ (ኤልሻዳይ) መሆኔን በማስረዳት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተገልጬላቸዋለሁ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በተሰኘው ቅዱስ ስሜ አማካይነት ግን አልተገለጥኩላቸውም።