ዘፍጥረት 32:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ ሁለቱን ሚስቶቹን፥ ሁለቱን ሴቶች አገልጋዮቹንና፥ ዐሥራ አንዱን ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ፤ ሁለቱን ሚስቶቹን እንዲሁም ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና ዐሥራ አንድ ልጆቹን ይዞ በያቦቅ መልካ ተሻገረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ሌሊትም ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹን፥ እና ዐሥራ አንዱን ልጆቹን ወስዶ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ዕቁባቶቹን ዐሥራ አንዱንም ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያች ሌሊትም ተነሣ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ባሪያዎቹን አሥራ አንድንም ልጆቹን ወስዶ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ። |
ነገር ግን ወደ ዐሞናውያን ግዛት አጠገብ ወይም ወደ ያቦቅ ወንዝ ዳርቻ ወይም ወደ ኮረብታማይቱ አገር ከተሞች ወይም እግዚአብሔር እንዳንደርስባቸው ወዳዘዘን እነዚህን ከመሳሰሉት አገሮች ወደ አንዲቱ እንኳ አልቀረብንም።
ለሮቤልና ለጋድ ነገዶችም ከገለዓድ እስከ አርኖን ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት ሰጠሁ፤ የደቡብ ወሰናቸውም የአርኖን ወንዝ አጋማሽ ሲሆን የሰሜን ወሰናቸው የዐሞናውያን ጠረፍ ክፍል የሆነው የያቦቅ ወንዝ ነው።
በሐሴቦን ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን ነበር፤ ግዛቱም የገለዓድን እኩሌታ በማጠቃለል፥ በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከምትገኘው ከዓሮዔር ተነሥቶ በዚያ ሸለቆ መካከል ያለችውን የዐሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ይደርስ ነበር፤
የዐሞንም ንጉሥ ለዮፍታሔ መልእክተኞች መልስ ሲሰጥ “እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ከአርኖን ወንዝ እስከ ያቦቅ ወንዝ ያለውን ምድሬንና የዮርዳኖስንም ወንዝ ወሰዱብኝ፤ አሁን ግን በሰላም መመለስ ይኖርባችኋል” አላቸው።