እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል” ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤
ዘፍጥረት 30:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ ዐድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት፣ ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል”። አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም፥ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፤ እንግዲህስ ከዛሬ ጀምሮ ባሌ ይወደድኛል ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፤ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም፦ እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፤ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፤ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው። |
እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል” ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤
ልያም “ባሌን የነጠቅሽኝ አንሶሽ፥ አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣልኝን እንኮይ መቀማት ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “ከልጅሽ እንኮይ ስጪኝና ዛሬ ሌሊት ያዕቆብ ካንቺ ጋር ይደር” አለቻት።
በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ። በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።
ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።
ሳኦልም እንደ ገና “ንጉሡ ስለ ልጁ ከአንተ የሚፈልገው ጥሎሽ ጠላቶቹን መበቀል እንዲችል አንድ መቶ ፍልስጥኤማውያን ገድለህ ሸለፈታቸውን እንድታመጣለት ብቻ ነው” ብላችሁ ንገሩት ሲል ባለሟሎቹን አዘዘ። ሳኦል ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲገደልለት በማቀድ ነበር።