Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 30:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ልያም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም ስጦ​ታን ሰጠኝ፤ እን​ግ​ዲ​ህስ ከዛሬ ጀምሮ ባሌ ይወ​ደ​ድ​ኛል ስድ​ስት ልጆ​ችን ወል​ጄ​ለ​ታ​ለ​ሁና” አለች፤ ስሙ​ንም ዛብ​ሎን ብላ ጠራ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ ዐድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት፣ ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል”። አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ልያም፦ እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፤ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፤ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 30:20
15 Referencias Cruzadas  

ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።


“ዛብ​ሎን ጫማ​ውን አዝቦ ይኖ​ራል፤ እር​ሱም እንደ መር​ከ​ቦች ወደብ ይሆ​ናል፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ሲዶና ይሰ​ፋል።


የልያ ልጆች፤ የያ​ዕ​ቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፤


በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ላይ ኃጢ​አ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም አይ​ግቡ።


በአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ሥር የነ​በ​ራ​ቸው እነ​ርሱ ከኤ​ፍ​ሬም፥ ብን​ያም ሆይ! በሕ​ዝብ መካ​ከል ከአ​ንተ በኋላ ወረዱ፤ አለ​ቆች ከማ​ኪር፥ የን​ጉ​ሥ​ንም ዘንግ የሚ​ይዙ ከዛ​ብ​ሎን ወረዱ።


ባር​ቅም ዛብ​ሎ​ን​ንና ንፍ​ታ​ሌ​ምን ወደ ቃዴስ ጠራ​ቸው፤ ዐሥር ሺህም ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ወጡ፤ ዲቦ​ራም ከእ​ርሱ ጋር ወጣች።


የዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች፤ ሳሬድ፥ አሎን፥ አሌል።


ልያም፥ “ባሌን መው​ሰ​ድሽ አይ​በ​ቃ​ሽ​ምን? አሁን ደግሞ የል​ጄን እን​ኮይ ልት​ወ​ስጂ ትፈ​ል​ጊ​ያ​ለ​ሽን?” አለ​ቻት። ራሔ​ልም “እን​ኪ​ያስ ስለ ልጅሽ እን​ኮይ በዚ​ህች ሌሊት ከአ​ንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠ​ቻ​ትም።


ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ባሌ ወደ እኔ ይጠ​ጋል፤ ሦስት ወን​ዶች ልጆ​ችን ወል​ጄ​ለ​ታ​ለ​ሁና” አለች፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራ​ችው።


ልያም ደግማ ፀነ​ስች፤ ስድ​ስ​ተኛ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደች።


ከዚ​ያም በኋላ ሴት ልጅን ወለ​ደች፤ ስም​ዋ​ንም ዲና አለ​ቻት።


ብዙ ማጫ አምጣ በሉኝ፤ በም​ት​ጠ​ይ​ቁ​ኝም መጠን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይህ​ችን ብላ​ቴና ግን ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ስጡኝ።”


አባ​ቷም እር​ስ​ዋን እን​ዳ​ይ​ሰ​ጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደና​ግል ማጫ ያህል ማጫ​ዋን ይስ​ጠው።


ሳኦ​ልም አላ​ቸው፥ “የን​ጉ​ሥን ጠላ​ቶች ይበ​ቀል ዘንድ ከመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይ​ሻም ብላ​ችሁ ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” አላ​ቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ይጥ​ለው ዘንድ አስቦ ነው።


ይረ​ግ​ሙም ዘንድ በጌ​ባል ተራራ ላይ የሚ​ቆሙ እነ​ዚህ ናቸው፤ ሮቤ​ልና ጋድ፥ አሴ​ርና ዛብ​ሎን፥ ዳንና ንፍ​ታ​ሌም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios