Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 68:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ። በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የሚመራቸው ትንሹ ብንያም ነው፤ በዚያ በብዙ የሚቈጠሩ የይሁዳ መሳፍንት፣ እንዲሁም የዛብሎንና የንፍታሌም መሳፍንት ይገኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እግዚአብሔርን በጉባኤ፥ የእስራኤል ምንጭ ጌታችንንም አመስግኑት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ላይ ኃጢ​አ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም አይ​ግቡ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 68:27
17 Referencias Cruzadas  

ሳኦልም “እኔ ከእስራኤል ነገዶች መካከል በተለይ ታናሽ የሆነው የብንያም ነገድ ተወላጅ ነኝ፤ በዚሁም ነገድ ውስጥ እንኳ የእኔ ቤተሰብ በጣም አነስተኛ ነው፤ ታዲያ እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለእኔ ስለምን ትነግረኛለህ?” ሲል መለሰለት።


ከዚያን በኋላ የእስራኤል መንግሥት በይሁዳ ላይ ያለውን ምቀኝነት ይተዋል፤ ይሁዳም በእስራኤል ላይ ያለውን ጠላትነትና ጥላቻ ያቆማል።


ገለዓድና ምናሴ የእኔ ናቸው፤ ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቊር ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።


የመንግሥታት መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር ይሰበሰባሉ፤ የምድር ገዢዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ናቸውና፤ እርሱ ከሁሉም በላይ ከፍ ያለ ነው።


ስለዚህም ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደተዘጋጀለት ስፍራ ለመውሰድ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አስጠራ፤


አንድ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች የተውጣጡ ጥቂት ሰዎች ዳዊት ወዳለበት ምሽግ ሄዱ፤


እግዚአብሔርም እስራኤልን በብንያማውያን ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረገ። በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከብንያም ወገን ኻያ አምስት ሺህ አንድ መቶ የጦር መሣሪያ የታጠቁ ሠራዊትን ገደሉ።


የዛብሎን ሕዝቦች፥ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጡ።


እኛ የአንድ ሰው ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ ጠፍቶአል፤ የመጨረሻ ታናሽ ወንድማችን በከነዓን ከአባታችን ጋር አለ’ አልነው።


ከብንያም ነገድ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፥


አበኔር ለብንያም ነገድ ሕዝብም ይህንኑ ተናገረ፤ ከዚያም በኋላ የብንያምና የእስራኤል ሕዝብ ለማድረግ የተስማሙበትን ጉዳይ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ።


እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል፤ እግዚአብሔርንም በጉባኤው ሁሉ ፊት አመሰግነዋለሁ።


በእስራኤል ስም የምትጠሩ፥ ከይሁዳ ወገን የሆናችሁ፥ እናንተ የያዕቆብ ልጆች! ይህን ስሙ። እናንተ በታማኝነትና በእውነት ሳይሆን፥ የእስራኤልን አምላክ እናመልካለን ትላላችሁ፤ በእግዚአብሔር ስምም ትምላላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios