መልካም ነገር አድርገህ ቢሆን ኖሮ ተቀባይነት አይኖርህም ነበርን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በበርህ ላይ ያደባል፤ በቊጥጥሩ ሥር ሊያደርግህም ይፈልጋል፤ ሆኖም አንተ ልታሸንፈው ይገባል።”
ዘፍጥረት 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቲቱንም፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቀትሽን፥ በምትወልጂበትም ጊዜ የምጥ ሥቃይሽን አበዛሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል። ለእርሱም ታዛዥ ትሆኚአለሽ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሴቲቱም አላት፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፥ በጭንቅ ትወልጃለሽ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሴቲቱም እግዚአብሔር አላት፥ “ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ከወለድሽም በኋላ ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ይገዛሻል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሴቲቱም አለ፤ በፀነሰሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ገዥሽ ይሆናል። |
መልካም ነገር አድርገህ ቢሆን ኖሮ ተቀባይነት አይኖርህም ነበርን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በበርህ ላይ ያደባል፤ በቊጥጥሩ ሥር ሊያደርግህም ይፈልጋል፤ ሆኖም አንተ ልታሸንፈው ይገባል።”
ከቤተሰቡ መካከል እጅግ የተከበረ ያዕቤጽ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እናቱ እርሱን በወለደች ጊዜ ከባድ የምጥ ጣር ደርሶባት ስለ ነበር “ያዕቤጽ” የሚል ስም አወጣችለት፤
አንተ የምታስተላልፈውም ዐዋጅ እጅግ ታላቅ በሆነው በዚህ በንጉሠ ነገሥት መንግሥትህ ግዛት ሁሉ በይፋ በሚነገርበት ጊዜ እያንዳንድዋ ሴት ባለጸጋም ይሁን ወይም ድኻ ባልዋን በአክብሮት ትመለከታለች።”
አሁንማ ከሊባኖስ መጥቶ በተሠራ የሊባኖስ እንጨት ውስጥ በሰላም ዐርፋችሁ ትኖራላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ወላድ ሴት የምጥ ጣዕር ሲይዛችሁ ምን ይበጃችሁ ይሆን?
ምጥ የያዛት ሴት የምታሰማውን ጩኸት የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የመጀመሪያ ልጅዋን የምትወልድ በካር ሴት የምታሰማውን ድምፅ የመሰለ ኡኡታም አዳመጥኩ፤ ይህም ድምፅ ኢየሩሳሌም ትንፋሽ አጥሮአት እጅዋን ዘርግታ “ወዮልኝ! ጠፋሁ! እነሆ ሊገድሉኝ መጡ!” እያለች የምታሰማው ጩኸት ነበር።
ሴት በምትወልድበት ጊዜ የምጥ ቀንዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ከወለደች በኋላ ግን በዓለም ላይ ሕፃን ስለ ተወለደ ከመደሰትዋ የተነሣ ጭንቀትዋን አታስታውሰውም።
ሚስት በሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ በእርስዋ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያለው ባልዋ ነው። እንዲሁም ባል በሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ በእርሱ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያላት ሚስቱ ነች።
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።