ይስሐቅም “ቀደም ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” አለው።
ዘፍጥረት 27:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከሰማይ የሚያረሰርስ ጠል ይስጥህ! ምድርህን ያለምልምልህ! እህልህንና ወይንህን ያብዛልህ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የሰማይን ጠል፣ የምድርንም በረከት፣ የተትረፈረፈ እህልና የወይን ጠጅ ይስጥህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል ከምድርም ስብ የእህልንም የወይንንም ብዛት ይስጥህ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል፥ ከምድርም ስብ፥ የእህልንም፥ የወይንንም፥ የዘይትንም ብዛት ይስጥህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል ከምድርም የእህልንም የወይንንም ብዛት ይስጥህ አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ |
ይስሐቅም “ቀደም ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” አለው።
አባታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ይምጡ፤ እኔም በግብጽ አገር ለም የሆነውን ቦታ መርጬ እሰጣቸዋለሁ፤ በቂ ምግብ አግኝተው በደስታ መኖር ይችላሉ።
የአባትህ አምላክ ይረዳሃል፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ከላይ ከሰማይ ዝናብን፥ ከምድርም ጥልቀት ውሃን በመስጠት ይባርክሃል፤ ብዙ ከብትና ብዙ ልጆችም ይሰጥሃል።
“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ሰሎሞንም በበኩሉ በኪራም ቤተ መንግሥት ውስጥ ላሉት ሰዎች ቀለብ የሚሆን ሁለት ሺህ ቶን ስንዴና አራት መቶ ሺህ ሊትር ንጹሕ የወይራ ዘይት በየዓመቱ ይሰጥ ነበር።
እንጨት ለሚቈርጡ ለሠራተኞችህ ስንቅ የሚሆን ሁለት ሚሊዮን ኪሎ ስንዴ፥ ሁለት ሚሊዮን ኪሎ ገብስ፥ አራት መቶ ሺህ ሊትር የወይን ጠጅና አራት መቶ ሺህ ሊትር የወይራ ዘይት እልክልሃለሁ።”
እናንተ ከላይ ያላችሁ ሰማያት! ጽድቅን እንደ ዝናብ አውርዱ፤ ደመናም ያርከፍክፈው፤ ምድር ትከፈት፤ ደኅንነትም ያቈጥቊጥ፤ እኔ እግዚአብሔር የፈጠርኩት ስለ ሆነ ጽድቅም ከእርሱ ጋር ይብቀል።”
ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።
ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ እህል፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አሕዛብ መዘባበቻ እንዲያደርጉአችሁ አልፈቅድም።
ከሞት የተረፉትም የእስራኤል ሕዝብ በብዙ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔር እንደሚልከው ጠልና በሣር እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ፤ ተማምነው የሚጠባበቁት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ይሆናል።
እህላቸውን በሰላም ዘርተው ፍሬውን ይሰበስባሉ የወይን ተክሎቻቸውም ያፈራሉ። በቂ ዝናብ ስለሚዘንብ ምድሪቱ ብዙ ሰብል ትሰጣለች፤ ከስደት ለተረፉት ሕዝብ ይህን ሁሉ በረከት እሰጣለሁ።
አፈሩ ለም፥ ምድሪቱም በደን የተሸፈነች መሆንዋን መርምሩ፤ አይዞአችሁ እዚያ ከሚገኘው ፍራፍሬ ይዛችሁ ኑ።” ወቅቱም የወይን ፍሬ መብሰል የጀመረበት ጊዜ ነበር።
እንደ ጓሮ የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የሆኑ አይሁድ ተቈርጠው ቢወድቁና እናንተ እንደ ዱር የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የሆናችሁ አሕዛብ በቦታቸው ተተክታችሁ የእነርሱን ሀብትና በረከት ተካፋዮች ብትሆኑ፥
እርሱ አንተን ይወድሃል፤ ይባርክህማል፤ ስለዚህም በቊጥር ትበዛለህ፤ የምትወልዳቸው ልጆች ይባረካሉ፤ የምድርህም ፍሬ ይባረካል፤ ስለዚህም ብዙ እህል፥ ወይንና የወይራ ዘይት ታገኛለህ፤ ከዚህም ጋር ብዙ የከብትና የበግ መንጋ ያበዛልሃል፤ ለአንተ ይሰጥህ ዘንድ ለቀድሞ አባቶችህ ተስፋ በሰጠው ምድር ላይ ይህን ሁሉ በረከት ይሰጥሃል።
ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው ሁሉም እስኪያልቁ ድረስ እስራኤላውያን በበረሓ ለአርባ ዓመት ተጓዙ። ለልጅ ልጆቻቸው ሊሰጥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ቃል ገብቶ የነበረውን በማርና በወተት የበለጸገውን ምድር በምድረ በዳ ያለቁት ልጆቻቸው እንደማያዩት አረጋግጦ ነበር።