ዕዝራ 2:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቤተ መቅደስ ሥራ ከተመደቡትም መካከል ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓሃ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ዓቁብ፥ ሐጋብ፥ ሻምላይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ አስና፥ መዑኒም፥ ነፊሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሉት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲሣራ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ የሲሐ፣ የሐሡፋ የጠብዖት ዘሮች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ የፂሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጣባዖት ልጆች የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናታኒም፤ የሲሓ ልጆች፥ የሐሡፊ ልጆች፥ የጠብዖት ልጆች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናታኒም፤ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ |
እንዲሁም ንጉሥ አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ከእስራኤል ልጆች መካከል ካህናት፥ ሌዋውያን፥ መዘምራን፥ በር ጠባቂዎችና የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ከዕዝራ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
እነርሱንም በካሲፍያ ለሚኖር ሕዝብ መሪ ወደ ሆነው ወደ ኢዶ በመላክ ኢዶና የቤተ መቅደስ ሠራተኞች የሆኑት ረዳቶቹ በቤተ መቅደስ የሚያገለግሉ ሰዎችን ይልኩልን ዘንድ እንዲነግሩአቸው አደረግሁ።
በተጨማሪም የቀድሞ አባቶቻቸው ሌዋውያንን ይረዱ ዘንድ በንጉሥ ዳዊትና በባለሟሎቹ ተሹመው የነበሩ ብዛታቸው ሁለት መቶ ኻያ የሆነ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ነበሩ፤ እነርሱም በየስማቸው ተመዝግበዋል።
የቀሩትም ሰዎች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች፥ የቤተ መቅደሱ መዘምራን፥ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና ለእግዚአብሔር ሕግ ታዛዦች የሆኑ በጐረቤት ከሚኖሩት የባዕዳን አገር ሕዝቦች ራሳቸውን የለዩ፥ ከሚስቶቻቸው፥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው ጋር፥
የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የኢየሩሳሌም ከተማ አንዱ ክፍል በሆነው ዖፌል ተብሎ በሚጠራው ኮረብታ ላይ ይኖሩ ነበር፤ ጺሐና ጊሽፓ ተብለው የሚጠሩም ሰዎች የእነርሱ አለቆች ነበሩ።
በሌሎች መንደሮችና ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤል ልጆች ካህናቱና ሌዋውያኑ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች በየመንደሮቻቸው ባላቸው ይዞታ ኖሩ። በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የይሁዳ ምድር መሪዎችም ስም ዝርዝር የሚከተለው ነበር፦