Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 11:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የኢየሩሳሌም ከተማ አንዱ ክፍል በሆነው ዖፌል ተብሎ በሚጠራው ኮረብታ ላይ ይኖሩ ነበር፤ ጺሐና ጊሽፓ ተብለው የሚጠሩም ሰዎች የእነርሱ አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች በዖፌል ኰረብታ ላይ ተቀመጡ፤ ሲሐና ጊሽጳ በእነርሱ ላይ ያዝዙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹም በዖፌል ተቀመጡ፤ ጺሓና ጊሽፓ በቤተ መቅደስ አገልጋዮች ላይ አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ናታ​ኒ​ምም በዖ​ፌል ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ሲሐና ጊስ​ፋም በና​ታ​ኒም ላይ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ናታኒምም በዖፌል ተቀምጠው ነበር፥ ሲሓና ጊሽጳ በናታኒም ላይ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 11:21
5 Referencias Cruzadas  

በየከተማው ወዳለው ይዞታቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ ካህናት፥ ሌዋውያን፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና ሌሎችም እስራኤላውያን ነበሩ።


ኢዮአታም የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ በር እንደገና ሠራ፤ በተጨማሪም በኢየሩሳሌም በሚገኘው ዖፌል ተብሎ በሚጠራው ኰረብታማ ቦታ የከተማ ቅጽሮችን በመሥራት ብዙ ሥራ አከናውኖአል፤


ለቤተ መቅደስ ሥራ ከተመደቡትም መካከል ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓሃ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ዓቁብ፥ ሐጋብ፥ ሻምላይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ አስና፥ መዑኒም፥ ነፊሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሉት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲሣራ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ።


ወርቅ አንጥረኛው ማልኪያ ተከታዩን መስመር ከቅጽሩ ማእዘን ሰሜናዊ ምሥራቅ ጫፍ አጠገብ እስካለው መቈጣጠሪያ ቅጽር በር በኩል የቤተ መቅደሱ ሠራተኞችና ነጋዴዎች እስከሚገለገሉበት ስፍራ ድረስ ሠራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos