ዘፀአት 6:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የሌዊ ልጆች ስሞች እንደ ትውልዳቸው ጌርሾን፥ ቀሃት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። |
ሥራውን እንዲቀጥሉ የተደረጉት ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፦ ከቀዓት ጐሣ፦ የዐማሣይ ልጅ ማሐትና የዐዛርያስ ልጅ ኢዩኤል፤ ከመራሪ ጐሣ፦ የዓብዲ ልጅ ቂሽና የይሀልኤል ልጅ ዐዛርያስ፤ ከጌርሾን ጐሣ፦ የዚማ ልጅ ዮአሕና የዮአሕ ልጅ ዔዴን፤ ከኤሊጻፋን ጐሣ፦ ሺምሪና ይዒኤል፤ ከአሳፍ ጐሣ፦ ዘካርያስና ማታንያ፤ ከሄማን ጐሣ፦ ይሒኤልና ሺምዒ፤ ከይዱቱን ጐሣ፦ ሸማዕያና ዑዚኤል።
ዓምራም ዮኬቤድ የተባለችውን የአባቱን እኅት አገባ፤ እርስዋም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት። ዓምራም በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነው።
ከሌዋውያን ነገድ ተወላጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓት፥ ሜራሪና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። የእነርሱም ዘሮች ሊብኒ፥ ኬብሮን፥ ማሕሊ፥ ሙሴ፥ ቆሬና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። ቀዓትም አሞራምን ወለደ።
የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ጐሣ ወጣ፤ ከሌዊ ነገድ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተከፋፈለ፤ እነዚህም ከተሞች የተወሰዱት ከይሁዳ፥ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ይዞታዎች ነበር፤