ዘፀአት 32:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም ይህን ባየ ጊዜ በወርቁ ጥጃ ፊት መሠዊያ ሠርቶ “ነገ ለእግዚአብሔር ክብር በዓል ይደረጋል” ሲል አስታወቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮን ይህን ባየ ጊዜ በወርቅ ጥጃው ፊት ለፊት መሠዊያ ሠርቶ፣ “ነገ ለእግዚአብሔር በዓል ይሆናል” ብሎ ዐወጀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም አየውና መሠዊያን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፦ “ነገ የጌታ በዓል ነው” ሲል አወጀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም በአየው ጊዜ መሠዊያውን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፥ “ነገ የእግዚአብሔር በዓል ነው” ሲል አወጀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም ባየው ጊዜ መሠዊያን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፦ ነገ የእግዚአብሔር በዓል ነው ሲል አወጀ። |
በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት የእስራኤል አምላክ የእግዚአብሔር ፋሲካ ለብዙ ጊዜ ብዛት ባለው ሕዝብ ስላልተከበረ ንጉሡና ሕዝቡ በሰሜን ከሚገኘው ከዳን በደቡብ እስከሚገኘው እስከ ቤርሳቤህ ለሚገኙ እስራኤላውያን በኢየሩሳሌም ተሰብስበው እንዲያከብሩት ዐዋጅ ይታወጅ ዘንድ ወሰኑ።
ሙሴም “ሕፃን ልጆቻችንና ሽማግሌዎቻችን ሳይቀሩ ሁላችንም እንሄዳለን፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን፥ በጎቻችንንና ፍየሎቻችንን፥ የቀንድ ከብቶቻችንንም ሁሉ እንወስዳለን፤ በምንሄድበት ስፍራ ለእግዚአብሔር በዓል እናደርጋለን” ሲል መለሰ።
እኔ እግዚአብሔር ያደረግኹላችሁን ሁሉ በማስታወስ ይህ ቀን መንፈሳዊ ክብረ በዓል ይሁንላችሁ፤ እርሱንም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ እንድታከብሩት ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ።”
እርሱም የወርቅ ጒትቻውን ሁሉ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፤ የቀለጠውንም ወርቅ በቅርጽ መሥሪያ ውስጥ አግብቶ የወርቅ ጥጃ አድርጎ ሠራው። እነርሱም “እስራኤል ሆይ! ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላካችን ይህ ነው!” አሉ።
በማግስቱ ሰዎቹ ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ እነርሱም ተቀምጠው ከበሉና ከጠጡ በኋላ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ።
“የእስራኤል ሕዝብ ለራሳቸው ታላላቅ ቤተ መንግሥቶች ሠርተዋል፤ እኔን ፈጣሪአቸውን ግን ረስተዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ብዙ የተመሸጉ ከተሞችን ሠርተዋል፤ ስለዚህ ከተሞቻቸውንና ምሽጎቻቸውን የሚያቃጥል እሳት እልክባቸዋለሁ።”
በዚያም ቀን የአምልኮ ስብሰባ እንዲሆንላችሁ ታውጃላችሁ፤ ምንም ሥራ አትሥሩ፤ ይህ በምትኖሩበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጆቻችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።
“የምግብ መባ፥ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህሉን ቊርባን፥ መሥዋዕቱንና የመጠጡንም ቊርባን፥ በየተወሰነው ቀን ወደ እግዚአብሔር ታቀርቡባቸው ዘንድ የተቀደሱ ስብሰባዎች እንዲሆኑ የምታውጁአቸው የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው።