ዘፀአት 19:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያው በመጀመሪያው ቀን ወደ ሲና በረሓ ደረሱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛው ወር እስራኤላውያን ከግብጽ ለቅቀው በወጡበት በዚያችው ዕለት ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሦስተኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሦስተኛውም ወር የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። |
መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ አምስተኛው ቀን፥ ከኤሊም ተነሥተው በሲና እና በኤሊም መካከል ወዳለው “ሲን” ተብሎ ወደሚጠራው ምድረ በዳ መጡ።
እግዚአብሔርም መልሶ “አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔ እንደ ላክኹህም ምልክት የሚሆንህ ይህ ነው፤ ሕዝቤን ከግብጽ በምታወጣበት ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እኔን ታመልኩኛላችሁ” አለው።
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን በሲና በረሓ ሳሉ፥ እግዚአብሔር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን እንዲህ ሲል አነጋገረው፦
እግዚአብሔር ‘ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ስለምፈልግ ሕዝቡን ሰብስብ’ ባለኝ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፊት በቆማችሁበት ቀን ‘በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእኔ እንዲታዘዙና፥ ልጆቻቸውም እኔን መፍራትን ያውቁ ዘንድ ያስተምሩአቸው’ ያለውን አስታውሱ።