Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ይህ ወር ለእናንተ የዓመቱ መጀመሪያ ወር ይሁንላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ይህ ወር ለእናንተ የወር መጀመሪያ፣ የዓመቱም መጀመሪያ ይሁንላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ ከዓመቱ ወሮችም የመጀመሪያ ይሁናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ይህ ወር የወ​ሮች መጀ​መ​ሪያ ይሁ​ና​ችሁ፤ የዓ​መ​ቱም መጀ​መ​ሪያ ወር ይሁ​ና​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 “ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 12:2
14 Referencias Cruzadas  

አርጤክስስ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፥ ኒሳን ተብሎ በሚጠራው የመጀመሪያው ወር ፑሪም ተብሎ የተሠየመው ዕጣ መጣል እንዲጀመርና አይሁድን ለማጥፋት የተጠነሰሰውን ሤራ በሥራ ላይ ለማዋል አመቺ የሚሆነው ወርና ቀን የትኛው እንደ ሆነ ተለይቶ እንዲታወቅ ትእዛዝ ሰጠ፤ በዕጣውም መሠረት አዳር ተብሎ የሚጠራው ዐሥራ ሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን እንዲሆን ተወሰነ።


እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን በግብጽ ምድር እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤


ከመጀመሪያው ወር ከዐሥራ አራተኛው ቀን ዋዜማ ምሽት ጀምሮ እስከ ኻያ አንደኛው ቀን ምሽት ድረስ ያልቦካ እንጀራ ትበላላችሁ።


ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ይህን ሥርዓት አስተምሩ፤ ይህ ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው በቤተሰቡ ደረጃ አንድ ጠቦት ይምረጥ።


ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።


በዚህ ቀን፥ የዓመቱ መጀመሪያ በሆነው በአቢብ ወር ግብጽን ለቃችሁ ወጥታችኋል።


ከግብጽ በወጣችሁበት በአቢብ ወር፥ እኔ ባዘዝኳችሁ አኳኋን የቂጣን በዓል አክብሩ፤ ይህ በዓል በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀኖች ውስጥ እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ፤ ለእኔ ልትሰግዱ በምትመጡበት ጊዜ መባ ሳትይዙ አትምጡ።


“ከግብጽ የወጣችሁት በአቢብ ወር ስለ ሆነ የቂጣን በዓል በመጠበቅ በየዓመቱ አክብሩ፤ እንዳዘዝኳችሁ በአቢብ ወር እስከ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።


ስለዚህ ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የመገናኛው ድንኳን ተተከለ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ምንም ነውር የሌለበት አንድ ወይፈን በመሠዋት ቤተ መቅደሱን ታነጻለህ።


“የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ፤ በዚህም በዓል አከባበር እስከ ሰባት ቀን ድረስ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትበላላችሁ።


“እግዚአብሔር የሚከበርበት የፋሲካ በዓል የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጀንበር ጠልቃ መሸትሸት ሲል ይጀመራል፤


“የጌታ የፋሲካ በዓል የሚከበረው የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ይሁን።


“አንተን ከግብጽ ምድር ያወጣህ ከአቢብ ወር ውስጥ በአንዱ ሌሊት ስለ ሆነ በዚህ ወር የፋሲካን በዓል በማድረግ እግዚአብሔር አምላክህን አክብር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos